Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
በማለት የኢየሱስን ስም ጠንከር አድርገሀ ብትጠራ ሰይጣን ሁለተኛ አይጠጋህም» በማለት አስተማሩት ከተማም በታማኝነት ይህንን በየቀነ ይለው ነበር ዳሩ ግን ሰይጣን በእግዚአብሔር ላይ እንድናምፅና እንድንበድል ሊያስገድደን አይቻለውም ምንጊዜም ስለምንሠራው ኃጢአት ሁሉ እኛ ተጠያቂዎች መሆናችንን መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ይህንን ነው።
መይም ሥጳጣናታ ፅሜፀና ምድሮ ያታ ቻታ ፅጳርረታ ሇፈጥሪዎጳሷና ያፍፖፓረኦ ታ ፅፊ ፅሎሮ ጎውያ ሯያታ ፅጳረታና ኋርታ ፖፈፖሮጳዔጳጋ ይህ ጥቅስ የሚያስተምረን ዝለዓለማዊ ከሆነው ከእግዚአብሔር በስተቀር ሁሉም ነገር የተፈጠረ መሆኑን ነው ኢየሱስ ዓለምንና በዓለም ላይ የምናየውን ሁሉ ፀሐይና ከዋክብት የመሳሰሉትን ሌሎችንም ሁሉ ፈጠረፁ እርሱ የማይታየውንም ዓለም ደግሞ ፈጥሮአል ይህ የማይታየው ዓለም እግዚአብሔርን በታማኝነት የሚያገለግሉ በጎ መላአክትም የሚገኙበት ነው እንዲሁም በእግዚአብሔር ላይ ያመፁትና ሕጉ በሕይወታቸው ገዢ እንዳይሆን የሚቃወሙት ክፉ መላአክትም በዚያ ይገኛሉ እነዚህ ዓመፀኞች መላእክት ሰይጣንና አጋንንት ይባላሉ ለሊ እግዚአብሔር በዘፍጥረት ምፅራፍ እንደተገለጸው የሚታየውን ዓለም ከመፍጠሩ በፊት የማይታየው የመናፍስቱ ዓለም ተፈጥሮ ነበር ኢዮብ እግዚአብሔር ዓለምን በሚፈጥርበት ጊዜ መላእክት በዚያ እንደ ነበሩ ይነግረናል ሒ በመጀመሪያ እንደ ተፈጠሩ መናፍስት ሁሉ ጻድቅ ነበሩ እግዚአብሔር በተፈጥሮአቸው ክፉ ወይም ርኩሳን መናፍስትን አልፈጠረም እግዚአብሔር ክፋትን እንደማይደግፍ ያዕቆብ ያሳስበናል በዘፍጥ ላይ እግዚአብሔር ፍጥረቱን ሁሉ የሚሜታየውንና የማይታየው ሁሉ ተመለከተና መልካም መሆኑን አረጋገጠ መ በመናፍስት ዓለም ከፍጥረት በኋላ በአንድ ወቅት ከጊዜ በኋላ አንዳንዶቹ ሰይጣንና አጋንንት ይህም በዘፍጥረት ምዕራፍ ከሚገኘው ታሪክ በፊት በእግዚአብሔር ላይ የተደረገ ዓመፅ ነበር ምንም አንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ዓመፅ በግልጽ ባይስረዳም የሰይጣንና የአጋንንት ውድቀት በትንቢተ ኢሳይያስ እና በትንቢተ ሕዝቅኤል በተዘዋዋሪ መብራራቱን ብዙዎች ምሁራን ያምናሉ ምክንያቱም ስለ ባቢሎን ንጉሥና ስለ ጢሮስ ንጉሥ የሚናገሩት ትንቢቶች ሰው የሆነ ንጉሥ ሊያደርግ ከሚችለው በላይ የሆነ ነገር የሚናገሩ ናቸው ስለሆነም እንደ አርሱ ክፉዎች እንዲሆኑ ኃይሉን የስጣቸውን ክፉውን መሪ ሰይጣንን ያመለክታል ብለው ስለሚያብራሩ ነው እነዚህ ጥቅሶች ሰይጣን በጣም የተከበረና እጅግ ውብ የሆነ የእግዚአብሔር መልአክ እንደነበረ ያስተምሩናል እርሱ «ኪሩቤል» ነበረ እግዚአብሔርን የሚያከብርና ፈቃዱን የሚፈጽም በአጠገቡ የሚቆም ልዩ የሆነ መልአክ ነበረ በመጀመሪያ ምንም ክፋት አልነበረበትም ነገር ግን ልክ እንደ ሰው ዲያብሎስም ቢሆን እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ወይም ላለመታዘዝ ምርጫ ነበረው እግዚአብሔርን በማገልገል ላይ ሳለ ትፅቢት በልቡ ውስጥ በቀ ሰይጣን እንደ እግዚአብሔር ለመሆንና ከእርሰ አኩል ሊሆን ፈለገ በኃይል ለመግዛትና ከተቀ መላእክትም ክብርና አምልኮ ለመቀበል ፈለገ በአግዚአብሔር ላይ ካመፀ በኋላ እግዚአብሔር ከሰማይ አባረረው እንግዲህ ትዕቢት ወደ ዓለም ኃጢአትን ስላመጣና የሁሉም ኃጢአቶች ሥር ስለሆነ አግዚአብሔር የትዕቢትን ኃጢአት እጅግ ይጠላል ኢሳ እንደ ሰይጣን በየጊዜው ኃጢአትን በምንሠራበት ጊዜ በልባችን እግዚአብሔርን «እግዚአብሔር ሆይ እኔ አንተ የምትወደውን ማድረግ አልፈልግም እኔ የፈለግኩትን አደርጋለሁ የሕይወቴ ጌታ እኔ ነኝ» እያልነው ነው በሰማይ ከነበሩት መላእክት ውስጥ ሲሶ የሚሆኑት ከሰይጣን ማመፅ ጋር ስለ ተባበሩ ከሰማይ መባረራቸውን የሚጠቁሙ አንዳንድ የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎች አሉ ራእይ ብ ለመጀመሪያ ጊዜ ክፋት ወደ ዓለም የገባው ያኔ ነው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሰይጣንና ርኩሳን መላእክቱ ዕቅዶቹን ለማፈራረስ በመፈለግ ከእግዚአብሔር ጋር በጦርነት ላይ ናቸው ሰይጣንና አጋንንት መናፍስት ናቸውእንደ እኛ አካል ባይኖራቸውም የራሳቸው ማንነት አላቸው በሰውና በእንስሳት ሊያድሩ ይትላሉ አጋንንት ሊያስቡ ሊያቅዱና ሊያታልሉ የሚችሉ አዋቂ የሆኑ ፍጥረታት ናቸው ማር ኛ ጢሞ ቁቱ ውስጣዊ ስሜት ስላላቸው ይፈራሉ ሉቃስ ያል እነዚህ ርኩሳን መናፍስት ከሰው ይልቅ ብርቱዎች ቢሆኑም ኃይላቸውም ሆነ እውቀታቸው ውስን ነው የእግዚአብሔርን ፅቅድ ሙሉ በሙሉ ሊያውቁ አይችሉም ሰይጣን ፍጹም አውቀት ቢናረው ኖሮ ድል የሆነበትን የኢየሱስን ስቅለት ባልፈቀደ ነበር ቆላ አጋንንት እኛ የምናስበውን ሁሉ እንኳ አያውቁቻ ፍጡራን መናፍስት ስለሆኑ በአንዴ በሁሉ ቦታ ሊገኙ አይችሉም ስለሆነም ሰይጣን በአንድ ቦታ በአንድ ጊዜ ለምሳሌ ወይ እዚህ ወይም በአሜሪካ እንጂ በአንድ ጊዜ በሁለቱም አገሮች ሊገኝ አይችልም ይሁን እንጂ መንፈስ ስለሆነ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ወይም ወደ ማንኛውም አገር እጅግ በፍጥነት ሊጓዝ ይትላል በተጨማሪም አብዛኛውን ሥራውን በየቦታው በሚገኙት በርካታ አጋንንት አማካይነት ያከናውናል ሰይጣንና አጋንንቱ በተለያየ የሥልጣን ተዋረድ የተደራጁ ይመስላል ይህም ልክ አንድ ጦር ከተራ ወታደር እስከ ጄነራል ያለ ዓይነት አደረጃጀት እንዳለው ማለት ነው ስለዚህ የክፉ መናፍስት ሠራዊትም በተለያየ በዚሁ ዓይነት የሥልጣን ተዋረድ የተደራጁ ናቸውቡ መጽሐፍ ቅዱስ የጨለማ ዓለም ገዥዎች አለቆችና ሥልጣናት የክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት በማለት በጨለማ ዓለም ያሉትን የመናፍስት ክፉ ኃይላት በየደረጃቸው ያስቀምጣቸዋል ኤፌ ሰይጣንና አጋንንቱ ፍጡራን ስለሆኑ መ በሙሉ በአግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ናቸወ እግዚአብሔር ሥልጣናቸውንና አለቅነታቸውን ይገድበዋል ሰይጣንና አጋንንት በአሁኑ ጊዜ በሁለት ዋና ዋና ቦታዎች ይገኛሉ አንደኛ አብዛኛዎቹ የወደቁ መላእክት ሰይጣንና አጋንንት «በአየር ላይ» ይኖራሉ ሴኤ ይህ ማለት ከእግዚአብሔር መኖሪያ ሰማይ ውጭ ሆነው በሰማያዊ ስፍራዎች ማለትም በሰማይና በምድር መዛል ይኖራሉ ማለት ነው ሰይጣን አሁንም ቢሆን እግዚአብሔር ወዳለበት ሰማይ ፄዶ በእግዚአብሔር ፊት ሰዎችን የመክሰስ ተግባር ያከናውናል ኢዮብ ራእይ በዚያ መኖር ግን አይችልም ብዙ ጊዜ ሥራውን ለማከናወን ወደ ምድር ይመጣል ሁለተኛ በእስር ላይ የሚገኙ ጥቂት የወደቁ መላእክት አሉ በኛ ሌጥ ኛ ጴጥ እና በይሁዳ ፅ ላይ ስለሚገኙት ከባድ ጥቅሶች ምሁራን ሦስት የተለያዩ አስተያየቶች አሏቸው ይህም ሀ አንዳንድ ምሁራን እነዚህ ጥቅሶች የሚያመለክቱት ስይጣንና አጋንንት በኃጢአት ስለ ወደቁበት ጊዜ ነው ይላሉ ከተፈጥሮ ቤታቸው ከሰማይ ተባርረው ከእግዚአብሔር መኖሪያ ተለይተው ጨለማ ወደ ሆነው እስር ቤታቸው ተወርውረዋል እነዚህ አጋንንት አሁንም ከእግዚአብሔርና ከልጆቹ ጋር በመፋለም ላይ ናቸው ይሁን እንጂ መጨረሻቸው ተወስኖአል ኢየሱስ ዳግም ሲመጣ ወደ ሲዖል ይወረወራሉ ኛ ጴጥ እግዚአብሔር እስከ ፍርዳቸው ቀን ያላመኑትን ሁሉ በእስር ላይ ያቆያቸዋል የሚል ተመሳሳይ ቃላት ስለሚጠቀም እነዚህ ምሁራን ይህንን አሳብ ይቀበሉታል ይሁን እንጂ ያላመኑ አሁንም ቢሆን በኃጢአታቸውና በእግዚአብሔር ላይ በማመጽ እየቀጠሉ ይንቀሳቀሳሉ ይኖራሉ ለ ሌሎች ምሁሆራን ደግሞ አንድ የአጋንንት ቡድን በአስር ላይ እንዳለ ያምናሉፊ ጥልቅ ጉድጓድ» እንጦሮጦስ ሲዖል ወይም ጥልቅ በተባለ ማቆያ ስፍራ ሆነው በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ፍርድ ወደ ገፃነመ እሳት እስከሚወረወሩበት ቀን ድረስ ይቆያሉ እነዚህ ክፉ መናፍስት ለም ደ ጉድጓዱ እን ተጣሉ በእርግጠኝነት አናውቅም አንዳንድ ምሁራን እነዚህ አጋንንት በዘፍጥረት ምዕራፍ ላይ «የእግዚአብሔር ልጆች» ተብለው የተጠሩና ከሰው ልጆች ጋር ወሲብ የፈጸሙ ናቸው ብለው ያምናሉ ዘፍጥ ይ ኢየሱስ በምድር ላይ እያለ አጋንንት በሚያወጣበት ጊዜ እስረኞቹ አጋንንት ወደሚገኙበት ወደ ጥልቁ እንዳይሰድዳቸው ይፈሩ ነበር በእነርሱ ላይ እግዚአብሔር የሚፈርድበት ጊዜ እንደሚመጣ አውቀዋል ሉቃስ ራ በዚያ ወቅት ኢየሱስ ወደ ጉድጓድ አንደ ወረወራቸው ግን ምንም ማስረጃ የለም ሒ በአስር ላይ ያሉት ሁለት የአጋንንት ቡድኖች ናቸው ብለው የሚያስቡ ሌሉች ምሁራን ደግሞ አሉ በጥልቁ ወኅኒ ቤት ያለው የአጋንንት ቡድን አንደኛው ነው በመጨረሻ ዘመን ለጥቂት ጊዜ እስኪለቀቁ ድረስ በዚያ ተይዘዋል ሪ ሌላው ቡድን እንጦሮጦስ በተባለው ስ ይክ ይገኛሉ በሆነ ምክንያት ከባድ ኃጢአት ስለሠሩ እግዚአብሔር በመጨረሻ ዘመን እነርሱንና ሰይጣንን ወደ ገዛፃነመ አሳት አእሳት ባሕሩ ውስጥ እስከሚሰድዳቸው ድረስ በዚያ ይቆያሉ ይላሉ ራአይ መጽኃፍ ቅዱፅዕ ሐይማጋጋም ሆን ለ ወደ ሰቅ ሦድጓድ ዳኃድፇምሳ ሥጳማ። ብለን መጠየቅና ማወቅ አለብን ይህን ካደረግን በኋላ በወጥመዱ እንዳንያዝ ራሳችንን ማዘጋጀት እንችላለን ከዲያብሎስ ተንኮሎች ሁሉ መጠንቀቅ እንዳለብን ሐዋርያው ጳውሎስ ይነግረናል ኛ ቆሮ የሰይጣን የመጨረሻ ዓላማ የአግዚአብሔርን መንግሥት መቃወምና የራሱን መንግሥት ማቋቋም ነው ሰይጣን የሚለው ስም ራሱ ሪፖቃዎሜ» ማለት ነው ይህም ሰይጣን ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ውጊያ ላይ መሆኑን የሚያንጸባርቅ እውነት ነው መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት ዓይነት መንፈሳዊ መንግሥታት እንዳሉ ያሳያል የብርፃን መንግሥት ተብሉ የሚጠራው የእግዚአብሔር መንግሥት አንዱ ነው የጨለማ መንግሥት የተባለው የሰይጣን መንግሥት ደግሞ ሌላው ነው ቆላ ሉቃስ የሐዋ አሁን በምድር ላይ ያለችው የእግዚአብሔር መንግሥት ወይም ግዛት ኢየሱስ ክርስቶስን አምነው አግዚአብሔርን ለመከተል የመረጡትን ሰዎች የያዘች ቤተ ክርስቲያን ናት በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል ጦርነት ሲደረ ብዙውን ጊዜ ሰይጣን በርትቶ የሚጋጠምበት ጦር ሜዳ በእግዚአብሔር ልጆች ልብና ሕይወት ውስጥ ነው በቤተ ክርስቲያናት ውስጥ ለምን ብዙ ችግሮች አማኞች ብዙውን ጊዜ በእግዚአብሔር ቃል መሠረት የማይኖሩበት ሁኔታ ለዚህ ጥሩ ማስረጃ ሊሆን ይችላል ሰይጣን ካመፀበት ፅለት ጀምሮ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየተዋጋ የራሱን መንግሥት ለማስፋፋት በርትቶ እየሠራ ነው አብዛኞቹ የሰይጣን ስሞች ይህን ያንጸባርቃሉ «የዚህ ዓለም አምላክ» ኛ ቆር ብ እንዲሁም «የዚህ ዓለም ገዥ ዮሒ ተብሎ ተጠርቶአል እንዲህ የተባለበት ምክንያት በዓለማችን ላይ በሚከናወኑት ነገሮች ላይ አርሱ ምን ያህል ተጽፅኖ እንዳለው ለማሳየት ነው በቀጥታም ሆነ በሐሰት አምልኮ አማካኝነትን ወይም በተዘዋዋሪ ዕግዚአብሔርንና መንገዱን በመቃወም ፍላጎቱን እንዲፈጽሙ ሰይጣን በሕዝቦች አስተሳሰብና ባህል ላይ ተጽዕኖ ያደርጋል ራእይ ሀ ዳንኤል ሰይጣን ከዓለም መንግሥታት በስተጀርባ እንዳለ ያሳያል በተለይ ወንጌል እንዳይስፋፋ ከሚከለክሉና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ስደትን ከሚያመጡ መንግሥታት በስተጀርባ ይገኛ ል ምናልባትም ኮሚኒዝም ጣዖት አምልኮና አስልምና የተንሰራፋባቸወ አማኞችን በኃይል የሚያሳደዱ አገሮች ሁሉ ሰይጣን ዓላማውን ለማሳካት የሚጠቀምባቸው ናቸው ለሊ ሰይጣን ስዎች ከሚከተሏቸው ሐሰተኛ ፃይማኖቶች በስተጀርባም አለ ጳውሎስ በኛ ቆሮ ላይ የጣዖት አምልኮ የአጋንንት አምልኮ መሆኑን ይናገራል ሰዎች ስለ እግዚአብሔር እውነተኛነት ሰምተው እስካላመኑ ድረስ በሴላ አምነት ውስጥ ቢገቡ ሰይጣን ጉዳዩም አይደለም እግዚአብሔር የለሾች ቢሆኑ ወይም ጣዖትን አምላኪዎች ወይም በዛፍ የሚያመልኩ ወይም «ኢየሱስ ብቻ» የሚለውን ኑፋቄ የሚከተሉ ሙሉ ስሕተት በሆነው የእስልምና ፃይማኖትም ወይም በወግ ብቻ ሆነው በስሜታዊነት ላይ በተመሠረተ የሐሰት ክርስትና ውስጥ ቢገቡ በእውነተኛ አምልኮ ላይ ያልተመሠረተ እስከሆነ ድረስ ሰይጣን ግድ የለውም ሰይጣን ከሐሰት ሃይማኖቶች ሁሉ በስተጀርባ ስለሆነ በእነዚህ ፃሃይማኖቶች ውስጥ ባሉት ሰዎች አምልኮ በተዘዋዋሪ ይከብራል ሒ ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ባልተመሠረቱ ባህላዊ ተግባሮች በስተጀርባም ይገኛል ለምሳሌ ሴቶች እንደ እንስሳት በሚቆጠሩበት ባህል ወይም ከአንድ በላይ ጋብቻ በሚዘወተርበትና እግዚአብሔር ለቤተሰብ ያለውን ሥርዓት በሚያፋልስ ባሕል ወይም ሸክላ ሠሪዎችንና አንጥረኞችን በሚያገልል ባሕል ወይም ትምህርትን ብቸኛ የችግሮች ሁሉ ፈቺ አድርጎ በሚቆጥር ባሕል ወይም ከፈለግከው ዓይነት ሰው ጋር ወሲብ ማድረግና ዘመናዊ መሆን ጥሩ ነው በሚሉ አስተሳሰቦች ጀርባ ሰይጣን አለ እነዚህ ሁሉ ሰዎች እግዚአብሔርን በማክበር እንዳይኖሩ ለማድረግ ሰይጣን ያመጣቸው ዓለማዊ ሥርዓቶች ምሳሌ ናቸው ሰይጣንና አጋንንት ሰዎችን ያታልላሉ ፍጥ የሐዋ ኛ ቆሮ ኛ ጢሞ ቁኸ ኢየሱስ ሰይጣንን «የሐሰት አባት» ያለው ሰይጣን እውነትን በማጣመም እንዴት ደስ እንደሚለው ለማሳየት ብሎ ነው ዮሐ ብ በዘፍጥረት ምዕራፍ ላይ «እባቡ» ሰይጣን እውነትን በማጣመም ሔዋንን አንዳሳሳታትና እርሷም ውሸትን በማመኗ ኃጢአት እንደሠራች እንመሰከታለን ሰይጣን የማታለልን ዘዴ በመጠቀም ያላመኑትን ሰዎች መንፈሳዊ ዓይኖች እያሳወረ የእግዚአብሔር እውነት ገብቶአቸው እግዚአብሔርን እንዳያመልኩት ያደርጋል ኛ ቆሮ ቁ ብዙ ጊዜ ሰይጣን ሰዎችን የሚያስተው ከአግዚአብሔር ቃል እውነትን ወስዶ ውሸት ከሆነው አሳብ ጋር በመደባለቅ ነው ያላመኑ ሰዎች የእግዚአብሔርን አውነት እንዳያምኑ ሰይጣን ያስታቸዋል ሰዎች ትክክል ናቸው ብለው እንዲከተሏቸው ማናቸውም የዓለም ታላላቅ ሃይማኖቶች እውነትን ከውሸት ጋር ያጣመሩ ናቸው አውነቱ ግን ሲታይ ሰይጣን የሚጠቀምባቸው ሆነው ይገኛሉ ሰዎች ከሚያምኑት ነገር ጋር እንዲስማማ በማድረግ ሰይጣን የማታለያ መረቡን ይዘረጋል ተአምራትን ከእውነት አብልጠው ለሚቀበሉ ሰዎች ተአምራትን ያሳያቸዋል ሰዎች በሰይጣን ውሸትን እያመኑ እንዲቀጥሉ ሰይጣን ለጠንቋዮች ለሐሰተኛ ነቢያት ለሐሰተኛ ተአምራት ሠሪዎች ሁሉ ተአምራትን እንዲያሳዩ ኃይሉን ይሰጣቸዋል ራአይ ብ ሰይጣን ባለው ጥበብና ኃይሉ እየተጠቀመ ከእግዚአብሔር ፍላጎት ውጭ እንዲኖሩ ያላመኑትን ያታልላቸዋል ሰይጣን ክርስቲያኖችንም ጭምር ለማታለል አውነት መሳይ ውሸትን ከአውነት ጋር ይደባልቃል ጳውሎስ እንኳ ሰይጣንና አጋንንቱ የብርፃንን መላእክት» መስለው ይቀርባሉ» ይላል ኛ ቆር ብ የሰይጣን ትምህርት ሁሉ ሁልጊዜ ጥሩና መንፈሳዊ ይመስላል በመጨረሻ ግን ሰዎችን ለእግዚአብሔር ክብር ከሚያመጣ ሕይዐት በጥበብ በመጠቀም አንዳንዴም ሰዎች ን እንዲናገሩ ያበረታታቸዋል ጠንቋዮች እና ሌሎች በአጋ የተያዙ ሰዎችም ቢሆኑ በልሳን እንደሚናገሩ የጋ ነው ሰዎች አስፈላጊ ለሆኑ እውነቶች መታዘዝን ትተው በአንድ እውነት ላይ ብቻ አንዲያተኩሩ ያደርጋቸዋል ለምሳሌ ሰይጣን አማኞችን ሲያታልላቸው እግዚአብሔር ትኩረት የሚያደርገው ስለ ክርስቲያናዊ አኗኗራቸው ሳይሆን ከልብ በሚሰጡት አምልኮ ላይ ብቻ መሆኑን ይነግራቸዋል ስለዚህ ብዙ ክርስቲያኖች ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተው ጮክ ብለው ይዘምራሉ ዳሩ ግን ሳምንቱን ሙሉ ይዋሻሉ ወይም ይሰርቃሉ ወይም ይለግማሉ ወይም ሰዎችን ያማሉ ወይም ደግሞ ወሲባዊ ኃጢአትን ይፈጽማሉ ሌሎች ደግሞ እግዚአብሔርን የሚያስደስተው መልካም ሥራና ወግ መጠበቅ ስለሚመስላቸው ከአግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙ ነት አይመሠርቱም ሰይጣን የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚቃረኑ ነገሮችን መልካም ሥነ ምግባር ባላቸው አማኞች አማካኝነት እንኳ ሳይቀር ይናገራል ለምሳሌ ኢየሱስ መሚሕ መሆኑን እግዚአብሔር ገልጾለት ከመሰከረ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ጴጥሮስ መልሶ ኢየሱስ መሰቀል እንደሌለበት ተናግሯል ማቴ መልካም የሚመስሉ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይስማሙ ምክሮችን በምንሰጥባቸው ጊዜያት ሁሉ ለሰይጣን ፈተና ተሸንፈን እርሱ እየተጠቀመብን ነው ማለት ነው ለምሳሌ «አማኝ ባይሆንም ልታገቢው ትችያለሽ በጣም የተማረ ስለሆነና ሀብታምም ስለሆነ ጥሩ ኑሮ ልትኖሪ ትችያለሽ መስክረሽለት ወደ ክርስቶስ ልትመሪው ትችያለሽ ሰይጣን የሚያታልለው ግለሰቦችን ወይም ቤተ ክርስቲያናትን ብቻ አይደለም ሕዝቦችን በሙሉ ሊያታልል ይችላል ራእይ ኑ የመንግሥታት መሪዎች እግዚአብሔር እንደሌለ አድርገው ሲያስቡና ሲመላለሱ ሰይጣን የማታለል ሥራውን ያከናውናል ኮሚኒስት መንግሥታት እግዚአብሔር ያሰለመናሩን እንዲያውጁና ሕዝቦች የራሳቸውን ፍትሐዊ ኅብረተሰብ ማዘጋጀት ይችላሉ በማለት መርቷቸዋል ወይም ሰይጣን ዲሞክራሲያዊ ካፒታሊስት የሆኑትን አገራት ይይዝና ሰዎች የፈለጉትን እንዲያደርጉ ነጻነት ቢሰጣቸውና ብዙ ገንዘብ ለማግኘት በተቻላቸው መጠን በርትተው እንዲሠሩ ቢበረታቱ የሰው ፍላጎት ሁሉ ይሟላል የሚል አሳብ እንዲያድርባቸው ያደርጋል እንዲሁም ሰይጣን «ፈታኝ» ነው ሉቃስ « ኛ ተሰ በወጥመድ አይጥን መያዝ ከተፈለገ አይጧን ሊማርካት የሚችል ጥሩ መብል በወጥመዱ ውስጥ መቀመጥ አለበት አይጧም የወጥመዱን አደገኛነት ትረሳና አሳቧ በምግቡ ጣዕም ላይ ብቻ ያተኩራል በዚሁ ዓይነት መንገድ ሰይጣን እኛን ሊያጠምደን እና በኃጢአት ውስጥ ሊጥለን ሲፈልግ እግዚአብሔር የማይወደውንና በፊታችን ጥሩ መስሱ የሚታየንን ነገር በማስቀመጥ ይፈትነናል እንዲሁም የድርጊቱ ውጤት በራሳችን በቤተሰባችን በአገራችን በይበልጥም ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ያስረሳናል ሰይጣን ሔዋንን ሲፈትናት ሞትን በተመሰከተ እግዚአብሔር የሰጣትን ማስጠንቀቂያ ከእግዚአብሔር ጋር እና ከባልዋም ጋር አንዲሁም ከዚህ ዓለም ጋር የነበራት ግንኙነት ሁሉ እንደሚበላሽ ረሳች ሸፍጥ ሰይጣን ኢየሱስን ኃጢአት እንዲሠራ በፈተነው ጊዜ እነዚህን ነገሮች በፈተናው ውስጥ ማካተቱን እናያለን በመጀመሪያ ኢየሱስ ዳግም እንዳይርበው ለማድረግ ኃይሉን በራስ ወዳድነት ተጠቅሞ ድንጋዩን ወደ እንጀራዳቦ እንዲለውጠው ሰይጣን ፈተነው በዚሁ መንገድ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ምርጥ ምርጡን እንዲበሉ ሰይጣን የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ይፈትናቸዋል ከመባ ገንዘብ በመውሰድ የፈለጉትን ገዝተው እንዲጠቀሙ ወዘተ ይፈትናቸዋል አማኞች ከጋብቻ ውጭ ወሲባዊ ርካታ እንዲያገኙ ወይም የሚፈልጉትን እንዲያደርጉ ወይም እንዲያጭበረብሩ ይፈትናቸዋል ሁለተኛ ሰይጣን በመጨረሻው ለራሱ የሚሆነውን ሁሉ ለማግኘት በተሳሳቱ መንገዶች እንዲጠቀም ኢየሱስን ፈተነው ሰይጣን ኢየሱስ እንዲሰግድለትና የዓለም ንጉሥ እንዲሆን ነገረው የእግዚአብሔር ዓላማ ግን ኢየሱስ በመጀመሪያ አንዲሞት ከዛ በኋላ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶች ጌታ እንዲሆን ነበር ብዙ ዋጋ እንዲያወጣልንና ብዙ ገንዘብን እንድና ልባችን እያወቀ ያልተጣራ እህል ወደ ገበያ ወስደን ለመሸጥ ብንሞክር ሰይጣን ኢየሱስን የፈተነውን ዓይነት ፈተና ፈተነን ማለት ነው ከእኛ ይልቅ ጎበዝ የሆነ ሰው የቤት ሥራችንን እንዲሠራልንና አርሱ በሠራው አኛ ጥሩ ነጥብ አንድናገኝ ብናደርግ በሰይጣን ተፈትነናል ማለት ነው ሥራ ላይ እንደተገኘን ለማስመሰል የሰዓት ፊርማ ፈርመን ቁርሳችንን ለመብላት ብንሄድ ያው በሰይጣን ፈተና ውስጥ ገባን ማለት ነው በእግዚአብሔር የተፈቀዱልንን ነገሮች የማወቅ ፍላጎት ጥሩ ሥራ ጥሩ ደመወዝ ክ የመሪነት ቦታዎች የመሳሰሉትን ለማግኘት በተሳ መንገድ አንድንጠቀም ሰይጣን ይፈትነናል እግዚአብሔር በማይፈቅደው መንገድ አማካኝነት እነዚህን እንድናሳድድ ሰይጣን ያበረታታናል ሦስተኛ ኢየሱስ የሰዎችን ክብር ያገኝ ዘን እግዚአብሔር እንዲከላከልለት ግድ እንዲለወ ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው ኢየሱስ ራሱን ከረዥሙ ቤተ መቅደስ ቢወረውርና መላአክት ደርሰው ቢያድኑት በቤተ መቅደሱ የነበሩ ስዎች ምን እንደሚሉ እስቲ ገምቱ። እምነትህ እኮ የእውነት አይ ቢሆንማ ኖሮ ኃጢአት ባልሠራህ» ነበር አያለ ሰይጣን ያንሾካሹካል የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር ብዙ ክርስቲያኖች የሰይጣንን ድምፅ በጣም እንደሚወደን አያስታውሱም ለኃጢአታችን ዋጋ በመስቀሉ ሳይ እንደተከፈለልን ይረሳሉ ሰማያዊ አባታችን የፍቅርና የምሕረት አባት መሆኑን ይዘነጋሉ ስለዚህ ብዙ አማኞች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሳትፎ የላቸውም በዚሁ ምክንያት ዋጋ ቢስ ክርስቲያኖች ሆነዋል ይባስ ብሎ ሌሎቹ እምነታቸውን ይክዳሉ ከዚህ የተነሣ የሰይጣን ክስ ተሳክቶለታል ማለት ነው ሰይጣን ነፍሰ ገዳይ ነው ዮሐ ብ ሆነ እርሱ የሚሠራው ክፉ ሥራው ሁሉ ለጥፋት ነው ኃጢአት ግንኙነትን ያበላሻ ገብተን አስካላደስነው ድረስ ኃጢአት በሠራን ቁጥር ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ኅብረት ይበላሻል ሰይጣን ኃጢአትን ከእግዚአብሔር ጋር የነበራት ኅብረት ብቻ ሳይሆ ከባሏ ጋር የነበራት ግልጽ ግንኙነት ተበላሽቶ ነበ እርስ በርሳቸው መካሰስ ጀመሩ ሰይጣን ሰዎች ውሸቱን ስምተውለት እና አርስ በርሳቸው በጎሣ ጦርነት ሲገዳደሉ ወይም ሕፃናትን በውርጃ ሲገድሉ ደስ ይለዋል እንዲሁም ደግሞ ሰይጣን ሰዎችን ስለ ጊዜያዊ አርካታ ብቻ በማሰብ በወሲባዊ ደስታ እንዲሳቡ ያደርጋሻውና ራሳቸውንም ንጽሐን ቻቸውን በኤድስ እና በሌሎች በሽታዎች ይገድላቸዋል የሰይጣንን ውሸት ሰምተን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ የሆነውን ነገር ስንፈጽም ከአካል ክፍላችን ውስጥ አንዱን እና በዙሪያችን ያሉትን እያጠፋን መሆኑን እናስታውስ ሰይጣን ስዎች ለእግዚአብሔር በሙላት እንዳይታዘዙ በመገደብና በእርሱ መንግሥት እንዲቆዩ ለማድረግ ሰዎች እርሱ እንዲሠራ የፈቀዱለትን እና ማናቸውንም አስፈላጊ ኃይል ሁሉ ይጠቀማል ሆኖም የመቆጣጠሩ ደረጃ ከሰው ወደ ሰው ይለያያል ሀ ሰይጣን በማያምኑ ላይ ያለው ተጽዕኖ በጨለማው ግዛቱ ውስጥ ሰዎችን ጠብቆ ለማቆየት ተግቶ የማያምኑት ልጆቹ የሰይጣንን ወጥመድ እንዳያምኑ ሰይጣን መንፈሳዊ ዓይኖቻቸውን አሳውሮአል ኛ ቆሮ ቱብቁ ብዙዎች ሰዎች ወንጌልን ተረድተው እንዳያምኑ ከባድ የሚሆንባቸው ለዚሁ ነው ስለሆነም መደነቅ የለብንም ከዚህ የባሰ ክፋትን እንዲያደርጉ ሰይጣን አሳባቸውንና ተግባራቸውን ለመቆጣጠር ይፈልጋል ሰይጣን የሰዎችን አእምሮ ተጠቅሞ ከሌላ ጎሣ የሆኑትን ሰዎችን እንዲጠሉ ያደርጋል በሚያሰክር መጠጥ ወይም በስሜት እራሳቸውን እንዲጎዱ ወይም ሴቶችን እንዲያባልጉና ልጆችንም እንዲበድሉ ይገፋፋቸዋል ሮሜ ጹ መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሕይወት ውስጥ እንደሚኖር አጋንንት ደግሞ በአንዳንድ ያላመኑ ሰዎች ውስጥ ያድራሉ አንዳንዴም የሰዎቹን ድምፅ በመጠቀም ይናገራሉ ያልተለመደ ኃይል ይሰጧቸዋል ወይም ደግሞ ያልተለመዱ አካላዊ ችግሮችን ያመጡባቸዋል ወዘተ ዐ ሰይጣን ቀጥተኛ አምልኮ መቀበል እንዲችል ይህ የአንድ ወይም የብዙ አጋንንት ልዩ ዛይማኖት መሪዎች ተስጥቶ ታያል በራእይ ውስጥ ይህ ዘንዶ የተባለው ሰይጣን አንድ ቀን ሥልጣኑን «ፀረ ክርስቶስ ለተባለው የፖለቲካ መሪ እንደሚሰጥ እናነባለን ከዚያም ሥልጣኑን ተአምራት እንዲሠራ የሃይማኖት መሪ ለሆነው «ነቢይ» ይሰጠዋል ሰይጣን ዛሬም እንኳን ብዙ በሆኑ የዛይማኖት መሪዎች አማካይነት በቀላል መንገድ ይህንን ተግባሩን እያከናወነ ነው ለምሳሌ ልዩ የሆነውን ኃይላቸውን ለሐሰተኛ ሃይማኖታቸው ወይም ለጥንቆላ ተግባራቸው የሚገለገሉት ጠንቋዮች ብዙ ጊዜ በአጋንንት ቁጥጥር ሥር ሆነው ኃይልን ከእነርሱ በመቀበል ነው ለ ይህ ትልቅ ቁጥጥር በሌሎች ባላመኑ ሰዎች ላይም ሊመጣ ይችላል ወደ ቤተ ክርስቲያናችን የሚመጡ ጋኔን የሰፈረባቸው ሰዎች አሉ ጋኔኑ በተለያዩ መንገዶች ራሱን መግለጽ ይችላል አንዳንዴ ባልታወቀ በሽታ አማካኝነት ይሆናል ሉቃስ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሕመምተኛውን መሬት ላይ እስከመጣል የሚያደርስ ጠቅላላ የአካል ቁጥጥር ሊሆን ይችላል ማር በሌላ ጊዜ ደግሞ ግለሰቡ ባልተለመደ ዓይነት ሁኔታ አኗኗር ይኖራል ሉቃስ ማሳለቢያ በሽታ ያላቸው ሰዎችና ባልተለመደ ዓይነት የሚኖሩ ሕመምተኞች ሰዎች ሁሉ ጋኔን ሰፍሮባቸዋል ከማለት መታቀብ አለብን ብዙ በሽታዎችና የሥነ ልቦና ችግሮች የሕክምና ችግሮች ናቸው ስለዚህ አንድ በሽተኛ ወይም ያልተለመደ ነገር የሚያደርግ ሰው በሚያጋጥመን ጊዜ ከተራ ሕመም የመጣ ነው ወይስ ከጋኔን የሚለውን መለየት አለብን ከጋኔን የመጣ ችግር ከሆነ ብዙ ጊዜ ሌሎች ምልክቶች አሉ በኃይል ኢየሱስን መጥላት ወይም ሰዎች ወደ ኢየሱስ ሲጸልዩ ትልቅ የፍርፃት ስሜት ሊታይበት ይችላል ሰይጣን ወይም ጋኔን በግለሰብ ላይ እንዲህ ያለ መቆጣጠር የሚያገኘው እንዴት ነው። በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል በሚካሄደው መንፈሳዊ ጦርነት ስለሚኖረን ቀጥተኛ አስተዋጽኦ መጽሐፍ ቅዱስ የሰጠን ፍንጭ የለም ለምሳሌ መልአኩን ለመርዳት ሲባል ዳንኤል ክፉውን መልአክ በመቃወም እንዲጸልይ አልተነገረውም ምንም እንኳ ሰይጣን አገልግሎቱን ለማደናቀፍ እየፈለገ መሆኑን ጳውሎስ ቢያረጋግጥም ክርስቲያኖች እንዲጸልዩለት የጠየቃቸው ድፍረት እንዲያገኝ ነበር ኛ ተሲ ኤፌ ሰይጣን እያደረገ ያለውን ለመገደብ እየተቃወማችሁ ጸልዩ አላላቸውም ይልቅ መሪአችንን ኢየሱስን በመከተል ትእዛዛቱን በመፈጸም በቅድስና በመኖር በተለይም ወንጌሉን ለሌሉች በመመስከር በታላቁ መንፈሳዊ ጦርነት ላይ ተጽዕኖ ልናደርግ እንችላለን ሰዎች ሲያምኑ ከሰይጣን ግዛት ወጥተው ወደ ክርስቶስ መንግሥት ይገባሉ የእግዚአብሔር ልጆች የሆንን ለሰይጣን ለዓለምና ለኃጢአት ተፈጥሮአችን እንቢ አንገዛም ስንል የሰይጣን ኃይል በእኛና በዙሪያችን ባለው ዓለም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳያሳድር አንገድበዋለን እንደሚባለው አንበሳ አጋዘንን ለመግደል ሲፈልግ መጀመሪያ ወደ እርሷ ይጠጋና ከፍተኛ ጩኸትን ያሰማል አጋዘንዋ ትበረግግና መሮጥ አንበሳውም በቀላሉ ይይዛትና በዚህ ዓይነት መንገድ ሰይጣን ች ልብ ውስጥ ፍርፃትን ሊፈጥር ይፈልጋል ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔርን በማመን እርግጠኞች ሆነን መኖር አንችልም ኛ ዮሐ ቁ ኛ ጢሞ ክርስቲያኖች በአምልኮ ሲጠመዱና ከጉባኤያቸው ጋንንትን ሲያስወጡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰይጣን የሚናገረውን በጭራሽ ባይመራመሩና ስለሚሠራው ሥራም ባያጠት መጽሐፍ ቅዱስን እንዳያጠኑ በማድረግ ስለአሸነፋቸው በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ደከሙ ማለት ነው በዚህ ሰይጣን ይደሰታል በርግጥ ከመጠን በላይ በሰይጣን ላይ ትኩረት መስጠቱ በዙሪ የሚያካሄደው አሠራሩን እንዳናይ ሰይጣን ዓይናችንን ሊያሳውርብን ይችላል ከሰይጣን ይልቅ በእግዚአብሔር ላይና በቃሉ ላይ የበለጠ ትኩረት መስጠት ይናኖርብናል ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ የሰይጣንን እንቅስቃሴዎ ቀላል በሆነ መንገድ ልንለያቸው የምንችለው እኛ እየተሳተፍንበት ስላለነው በእግዚአብሔርና በሰይጣን መፃከል ስላለው ውጊያ መጽሐፍ ቅዱስ አንዳንድ ቁልፍ የሆኑ ሐቆችን ያሳያል ምንም እንኳ ሰይጣን ኃይለኛ አንበሳ ቢሆንም አጋንንትም ሁሌ በዙሪያችን ቢገኙም እኛ በአግዚአብሔር መላእክት ሠራዊት ታጥረናል የሶርያ ሠራዊት ኤልሳዕንና አገልጋዩን ሊማርካቸው ሲመጣ የብርቱ መላእክት ስውር ሠራዊት እንዲያይ እግዚአብሔር የአገልጋዩን ዓይኖች ገለጠ ኛ ነጊ እነዚያ የእግዚአብሔር መላእክት ዛሬ እኛንም እየረዱ ናቸው ዕብ ብ የእግዚአብሔር መላእክት ከሰይጣንና ከአጋንንት የበለጠ ኃይለኞች ስለሆኑ ሰይጣንን መፍራት የለብ በዚህ መንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ ብቻችንን አይደለንም እኛ በውስጣችን የሚኖር መንፈስ ቅዱስ አለን እርሱ እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ደግሞ ከሰይጣንና እርሱ በእኛ ላይ ሊያመጣ ከሚሞክረው ጥቃት የበለጠ ኃይለኛ ነው በኛ ዮሒ ቱብ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን በጭራሽ መርሳት የለብንም ከሁሉም ይበልጥ ኃይለኛ የሆነው የነገሥታት ንጉሥ ልጆች ነን ላ ተራና ደካሞች ሰዎች አይደለንም ልጆቹ ስለሆንን እግዚአብሔር በጥንቃቄ እየጠበቀን ነው እኛን ለመውጋት ከሚሞክረው ከመናፍስቱ ዓለም ሳይቀር ይጠብቀናል የእግዚአብሔር ልጆች እንደ መሆናችን መጠን በጥበቃው በእአንክብካቤውና በፍቅሩ ላይ መተማመን ይገባናል ፋፈ እግዚአብሔር ሰይጣንና አጋንንቱን በቅርበት ይቆጣጠራቸዋል ሊያደርጉት በሚችሉትም ላይ ገደብን ያበጃል ኢዮብ ዱጻ እግዚአብሔር ዓላማውን ለማስፈጸም በማንኛ ውም ፍጥረት ይጠቀማል በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት እንዲጎለብት ሰይጣንና አጋንንቱን በአማኞች ላይ አንዳንድ ነገሮችን እንዲያደርጉ ይፈቅድላቸዋል ዳሩ ግን የአግዚአብሔር ልጆችን እንዳያጠፋ እግዚአብሔር ሰይጣንን ይገድበዋል ሉቃስ አማኞችን ለማረምና ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ እግዚአብሔር ሰይጣንንና የሚያመጣውንም ጥቃት ይጠቀማል ዐኛ ቆሮ ኛ ቆሮ ኛ ጢሞ እግዚአብሔርና ሰይጣን በዚህ ዓለም ላይ ያሉ ሁለት ተመጣጣኝ ኃይላት እንዳልሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያሳያል እንዲያውም አንድ ታላቅ ኃይል ብቻ እንዳለ እርሱም አግዚአብሔር መሆኑን ነው የሚያሳየው ሰይጣን ክፉ ሥራዎቹን በሚገድብበት በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ነው ያለው እግዚአብሔር እጅግ ታላቅ ስለሆነ ሰይጣን የሚያደርገውን ማንኛውንም ክፋት የመጨረሻ ዓላማው ማስፈጸሚያ እንዲሆን ለበጎ ይለውጠዋል ታሪክ ሲደመደም እግዚአብሔር ሰይጣንን በቀላሉ ያሸንፈውና ወደ እሳት ባሕር ይጥለዋል ራአይ ኢየሱስ ሰይጣንንና ኃይላቱን ምን አደረጋቸው። በእርግጥ የእግዚአብሔርን ነበረ ሰይጣን ጴጥሮስን ለማሸነፍ የነበረውን ችሎታ ውሱን እንዲያደርገው ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር አብ ጸለየ ጴጥሮስ ኢየሱስን ይክደው ይሆናል ሆኖም ግን የጴጥሮስ ውድቀት ዘለቄታ ያለው እንዳይሆን ኢየሱስ ሻረው ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ ንስሐ ገብቶና ተመልሶ ኢየሱስን በመከተል ለቁም ነገር አገልግሎት እንደበቃ ነው ሰይጣን እኛ ንም ለማጥቃት ሲሞክር እንዲህ ያለ ነገር እንደሚደርስብን ጥርጣሬ የለውም እግዚአብሔርን መጠየቅ አለበት ሊቀ ካህናችን የሆነው ኢየሱስ ጥቃቱ ውሱን እንዲሆን ይጸልያል እንዲሁም ሰይጣን በአማኞች ላይ ሊያመጣ የሚችለውን የፈተና መጠን እግዚአብሔር መወሰኑን ይቀጥላል ስለዚህ ሰይጣን ነፃ ሆኖ የአግዚአብሔርን ልጆች ሊጎዳ እንደማይችል መጽሐፍ ቅዱስ ያሳያል ካለ እግዚአብሔር ፈቃድ ሰይጣን እንግዲህ ሊያሳምመን ወይም አደጋ እንዲደርስብን ወይም እንድንሞት ሊያደርግ አይችልም ሰይጣን እንዲያጠቃን እግዚአብሔር ሊፈቅድለት ይችላል ወይም እንዲጎዳን ብሎ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ሊያደርግበት ይችላል እግዚአብሔር ሰይጣን እንዲያጠቃን ሲፈቅድለት ግን ሁል ጊዜ መለኮታዊ ዓላማን ተመርኩዞ ነው ከኢዮብ ምሳሌነት እንደምንረዳው እምነታችን ንጽሕ እንደሆነ ለሰይጣን ለማሳየት ሊሆን ይችላል ኢዮብ ዴ እምነታችን ይበልጥ ነጽቶና ከወርቅ ይበልጥ ውድ ሆኖ እንዲገኝ የመግለጽ ዓላማም ሊኖረው ይችላል ኛ ጴጥ ሬኻ ለበለጠ ተግባራዊ አገልግሉት የሚያዘጋጀን ዓላማም ሊኖረው ይችላል ዐኛ ቆሮ እንደ ጳውሎስ በራሳችን ኃይል ሳይሆን ትሕትናን ተምረን በአግዚአብሔርና በኃይሉ እንድንተማመን እንዲያደርገን ብሎም ሊሆን ይችላል ኛ ቆር እግዚአብሔር ዋና ተቆጣጣሪ ሆኖ እኛ እንድናድግ ሊረዳን ብሎ ሰይጣንን እንደ መሣሪያ ይጠቀምበታል ስለዚህ መከራ ሲመጣብን እግዚአብሔርን በማክበር የሰይጣንን ጥቃት ለመመከት የሚያስችለን ኃይልና ብርታትን እንዲሰጠን እንድንጸናና እንድናድግ እግዚአብሔርን መለመን አለብን ሰይጣን እኛን የሚያጠራ የአግዚአብሔር መሣሪያ መሆኑን ለማስቆም ምን ማድረግ እንደሚገባን መጽሐፍ ቅዱስ አያስተምረንም ሰይጣን በሕመም እንዳያጠቃን ወይም ስደት እንዳያመጣብን ወዘተ በመቃወም እንድንጸልይ ፍጹም አልተነገረንም ከዚህ ይልቅ ልንጸልይ የሚገባን ወደ እግዚአብሔር ነው እነዚህ የመክራ ጊዜያት ከመድረሳቸው በፊት እግዚአብሔር እንዲሰውረን መጸለይ እንችላለን ማቴ እግዚአብሔር እነዚህን «የሰይጣን እሾኮች» እንዲነቅልልን በጥቃቱ ጊዜ መጸለይ እንችላለን ሰይጣን ያጥቃ አያጥቃ የሚለው ውሳኔ ግን የእግዚአብሔር ሥልጣንና መብት ይሆናል ሰይጣን ማጥቃቱን እንዲቀጥልበት መፍቀዱ የእግዚአብሔር ፍላጎት ሊሆን ይችላል ኛ ቆሮ ወይም ጸሎታችንን ስምቶ ከሰይጣን የሕመም ጥቃት ለጊዜው እንድንርቅ ሊረዳን ይችላል ከሰይጣን ስደትም ሆነ ከሞት እንደዚሁ ለጊዜው ሊያርቀን ይችላል ዳሩ ግን ክርስቲያኖች ሊገባቸው የሚገባው ነገር እንዲህ ያሉ በሰይጣን በኩል የሚመጡ ጥቃቶች እኛን ወደ ክርስቶስ ተምሳሌት በመቀየር ለአገልግሎት በይበልጥ ጠቃሚ ሊያደርጉን የሚችሉ እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ የሚጠቀምባቸው መሣሪያዎች መሆናቸውን ነው ሁለተኛ ሰይጣን ምንጊዜም ቢሆን ሊፈትነን ሥልጣን አለው ይኸውም እግዚአብሔርን እንድንበድል ሊያግባባን በመሞክር ነው የኃጢአት ተፈጥሮአችን ራስ ጠዳድነትና ዓመፀኛነት እንዲኖረው ይገፋፋዋል ለኢየሱስ እንዳደረገው ሁሉ ዓለም ጥሩ ነው ብላ የምታስተምረውን ነገር ያሳየናል እነዚህንም እግዚአብሔር በማይፈቅደው መንገድ እንድናገኛቸው ይነግረናል ዳሩ ግን ሰይጣን በእግዚአብሔር ላይ እንድናምፅና እንድንበድል ሊያስገድደን አይቻለውም ምንጊዜም ስለምንሠራው ኃጢአት ሁሉ እኛ ተጠያቂዎች መሆናችንን መጽሐፍ ቅዱስ ሁሌ ያስተምረናል ለሰይጣን ፈተናዎች መሸነፍ የራሳችን ምርጫ ነው ለሰይጣን ጥቃት አንበገርም ብለን ሰይጣንን የመቃወም ኃላፊነት የተሰጠን በዚህ ዙሪያ ነው ይሁን እንጂ የሰይጣንን ፈተናዎችም እንኳ ቢሆን እግዚአብሔር እንደሚቆጣጠራቸው ተነግሮናል ከዓቅማችን በላይ በሆነ ፈተና እንዲፈትነን እግዚአብሔር ለሰይጣን እንደማይፈቅድለት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል በእርሱ ላይ ከተማመንን እግዚአብሔር ፈተናውን የምናሸንፍበት መንገድ ያዘጋጅልናል ኛ ቆሮ ኣ ራሳችንን ከሰይጣንና ኃይላቱ የምንከላከለውና የምናሸንፋቸው እንዴት አድርገን ነው። ስለዚህ ነገር በጣም ግልጽ አድርጎ የሚነግረን የአዲስ ኪዳን ክፍል ኤፌ ነው ሀሁ መንፈሳዊ ውጊያን በተመለከተ ሁለት ዐበይት መርሖዎች የመንፈሳዊ ውጊያ ግብ «መጽናት» ነው በሰይጣን ተሸንፈን ኃጢአት ውስጥ መውደቅ ወይም ከጥቃቱ መሸሽ የለብንም ከዚህ ይልቅ በጽናት ኑሮን መኖር ሰይጣንን ተግተን ንዋጋ ጳውሎስ አያሳስበንም ከዚህ ይልቅ ትኩረት ሰጥቶ የሚናገረው ዋናው ሥራችን መሆን ያለበት ሰይጣን የሚያደርስብንን ጥቃት መቋቋም እንደሆነ ነው እኛ ሰይጣንን በተዘዋዋሪ የምንዋጋው የወንጌሉን እውነት ለሌሎች በማካፈል ነው ሰዎች ሲያምኑ የሰይጣንን የጨለማ ግዛት ትተው ብርዛን ወደሆነው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባሉ ደግሞም አዲሶቹ አማኞች የእግዚአብሔርን ቃል በተማሩ ጊዜ አሳባቸውንና ድርጊታቸውን እግዚአብሔር ከሚፈልገው ነገር ጋር ስለሚያጣጥሙት ሰይጣን በቀላሉ ሊያሸንፋቸው አይችልም ሰይጣንን የምንቋቋምበት ኃይል የሚመጣው ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳልሆነ መገንዘብ ይኖርብናል «በእግዚአብሔርና በብርቱ ኃይሉ ውስጥ መጽናት» አለብን መንፈሳዊ ውጊያችንን የምናሸንፈው በኃይላችን ሳይሆን በኢየሱስ ኃይል ላይ በመተማመን ነው ምንም እንኳ ጳውሉስ በሰይጣን ላይ ድል እንድናደርግ ከእግዚአብሔር ጋር በመተባበር አንዳንድ ልናደርጋቸው የሚገባን ነገሮች እንዳሉ ቢያሳየንም ሳንወድቅ ጸንተን ለመቆም የምንችለው ከእግዚአብሔር ዘንድ በሚመጣው ኃይል መሆኑን አረጋግጦ ያስታውሰናል ሰይጣን ከእኛ የበለጠ ብርቱና ጥበበኛ ነው ስለዚህ ድል ልንቀዳጅ የምንችለው የኢየሱስ ኃይል ሲኖረን ብቻ ነው ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሁለት ሐቆች እንዳሉ ጳውሎስ ያረጋግጥልናል አንደኛ ሰይጣንን የምናሸንፍበት ኃይል የሚወሰነው ከኢየሱስ ጋር ባለን ግንኙነት ወይም ቅርበት ነው በጸሎትና የእግዚአብሔርን ቃል በማጥናት ከኢየሱስ ጋር የቅርብ ግንኙነት ካለን ኃይሉ ዝግጁ ይሆንልናል በኢየሱስ ኃይል በርትተን ለኢየሱስ ክብር በሚያመጣ መንገድ ላይ እንድንራመድ በቆላ ጳውሎስ ለእኛ አማኞች እየጸለየ መሆኑን ይነግረናል እንዲህ ዓይነቱ የቀረበ ግንኙነት ከኢየሱስ ጋር ከሌለን ኃይሉም አይኖረንም በቀላሉ ደግሞ በሰይጣን ተሸናፊዎች እንሆናለን ሁለተኛ ኢየሱስ ብርቱ ኃይል ስላለው በሰይጣን ላይ ድልን መቀዳጀት ይቻላል ኢየሱስ ሥልጣን ሁሉ እንደተሰጠው ተናግሮአል ማቴ ፌ ኢየሱስ ከሰይጣን በእጅጉ ይበልጣል እርሱ ሰይጣን የሚያደርገውን ሁሉ ወሰን ያበጅለታል ሰይጣንን ለመቋቋም እንድንችል ኢየሱስ ብርቱ ኃይሉን መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በእኛ ውስጥ ፈተናው ብቻችን የምንጋፈጠው የሰይጣንን ፈተና አሸንፎ እንዲወጣ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን እንደረዳው ሁሉ እንዲሁም ሰይጣን የሚያመጣብንን ጥቃት እንድናሸንፍ መንፈስ ቅዱስ እኛንም ይረዳናል እንግዲህ በእነዚህ እውነቶች ላይ ተመሥርቶ ነው ጳውሎስ ልናሸንፈው ና በሕይወታችን ላይ እንደማይመጣ የነገረን ኛ ቆሮ በጉልበታችን ሰይጣንን ለመቋቋም ስንሞክር ብዙ ጊዜ ከሽፎብናል የሰይጣንን ጥቃት አውቀን እንድናሸንፈው ጥቃት ባጋጠመን ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ኃይሉን እንዲሰጠን መለመን ያስፈልገናል ለሌ ለውጊያው የሚሆን ትክክለኛ መሣሪያ በመያዝ ራሳችንን መከላከል ይገባል አንዳንዴ የመጀመሪያው መከላከያችን ሰይጣንን ከአኛ እንዲርቅ «የማዘዣ» የጸሎት ኃይል ይመስለናል ስለዚህም ብዙ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎታችን መጀመሪያ ላይ ሰይጣንን እንዲፄሄድልን እናዝዘዋለን ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ይህንን ነው። ራሱን የሚከላከልበት ልዩ መሣሪያ ተስጥቶት ነበ እንዲዋጋበት ደግሞ ጠመንጃ ተስጥቶት ነበ በተመሳሳይ መንገድ ጸሎት በመንፈሳዊ ውጊያችን ቁልፉ ቢሆንም ቅሉ ሰይጣንን ልንወጋበት የሚያስችለን እግዚአብሔር ልዩ የሆነ መሣሪያ ሰጥቶናል ይህም መሣሪያ ሰይጣን አማኝን ከሚያጠቃበት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ለዚያ ተብሎ የተዘጋጀ ነው በኤፌ ፋ ላይ ጳውሎስ መንፈሳዊ እንደምናሸንፍ ለማስረዳት ሲል የጦር መሣሪያ እንደ ምሳሌ ሀ የእውነት ቀበቶ ይህ መሣሪያ በመጀመሪያ የተጠቀሰው ውሸታሙን ሰይጣንን የምንዋጋበት እጅግ አስፈላጊ ዕቃ ስለሆነ ነው ቀበቶ ለሮማውያን የጦር ትጥቃቸው ማዕሪከል ነው ሲሮጡም ሆነ ሲዋጉ ልብሳቸው ሱሪያቸውን አንዳይወልቅ ጥብቅ አድርጎ ይይዝላቸዋል ሰይፋቸውንም ይይዝላቸዋል ሌሎቹም ትጥቆች እንደ ጥሩር የመሰለው ከእርሱ ጋር የተያያዙ ናቸው በዚሁ ዓይነት እውነት ደግሞ ሰይጣንን የምንቋቋምበት የእኛ ማእከላዊ መሣሪያ ነው ጳውሎስ የሚለው እውነትን ማወቅ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ነው ይህም ማለት አማኞች የእግዚአብሔርን ቃል ማወቃቸውና መታዘዛቸው እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ነው የሰዎች አሳብ ጥሩም ሆነ መጥፎ ወስደን ሥራ ላይ ማዋል የለብንም ጸንተን ሰይጣንን መቋቋም የምንችለው ስለ አግዚአብሔር ያለውን አውነት ስናውቅና አውቀንም ስንታዘዘው ነው ከሰዎችም ጋር ሆነ ብቻችንን የማንለወጥ እውነተኛ ቅን ወንዶችና ሴቶች መሆን አለብን እግዚአብሔር ከውስጣዊ ማንነታችን እውነትን አንደሚሻ ዳዊት ተናግሮአል መዝ እኛ እውነተኞች ልንሆን ይገባል ራሳችንን መሆን እንጂ ሌሎችን ለመሆን ማስመሰል የለብንም አማኞች ለራሳቸው «እውነተኞች» መሆን ያስፈልጋቸዋል ብርታታችንና ድካማችንን ማወቅ ያስፈልገናል እውነት የምንናገር መሆን ይገባናል ሐሰትንና አውነትን ቀላቅሎ መናገር ከሰይጣን እንጂ ከእግዚአብሔር አይደለም እውነትን አለማመን ወይም በቅንነት አለመኖር ወይም ደግሞ እውነትን አለመናገር ማለት የጦር ትጥቃችንን በአግባቡ አልለበስነውም ማለት ሲሆን ይህ ደግሞ ሰይጣን እንዲያሸንፈን ቀላል ይሆንለታል ማለት ነው ሌ ጥሩር በወታደር ደረት ላይ ሆኖ የሕይወቱ ዋና ብልቶች የሆኑትን ልብንና ሆድን የመሳሰሉትን ሁሉ የሚሸፍን የጦር ዕቃ ነው በዚሁ ዓይነት መንገድ ጽድቅ ቀጥተኛ ከሆነው የሰይጣን ጥቃት ይሸፍነናል ይህ ጽድቅ ሁለት ነገሮችን ያመለክታል አንደኛ ከዳንን በኋላ ከእግዚአብሔር የምናገኘው ጽድቅ አለ ሰይጣን ከሳሻችን ብዙ ጊዜ በኃጢአተኝነታችን እንድንዋጥ ያደርገናል ዳሩ ግን ማስታወስ የሚገባን በኢየሱስ ባመንን ጊዜ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን እንድናገኝ የሚያደርገን ጽድቅ ተሰጥቶናል ሮሜ ፋ ሁለተኛ እግዚአብሔርን በመታዘዝ የምናደርጋቸው የጽድቅ ሥራዎች አሉ አነዚህ የጽድቅ ሥራዎ አርስ በርስ መዋደድን ሰዎች ሲበድሉን ይቅር ማለ ድፃ መርዳትንና ሌሎችን ሊያጠቃልሉ ይችላሉ ከሰይጣን ጥቃት የምንከላከልበት ምርጥ መከላከያ ሕያው እምነት ነው እግዚአብሔር በሚከብርበት መንገድ ከኖርን ሰይጣን ሊፈትነንና ሊጎዳንም ቢሞክር ቀላል አይሆንለትም ሰይጣን አሳባችንን ለውጦ የእርሱን ውሸት እንድናዳምጥ ቀላል የሚሆንለት ሥራ ፈቶች ስንሆን ወይም በንቃት ኢየሱስን ሳናገለግለው ስንቀር ነው የአሁኑ ዘመን ወጣቶች ትጉሕ በመሆን ኃይላቸውን በሞላ በአግዚአብሔር አገልግሎት ላይ ማዋል ይገባቸዋል ቁጭ ብለው መዘመርና መጸለይ ብቻ በቂ አይደለም መክ ሒ ጫማ ወታደሮች ወፍራም ሶል ያለው ነጠላ ጫማ ያጠልቁ ነበር እነዚህን ያደረገ ወታደር እግሮቹ ሳይጎዱ እሾፃሃማና ድንጋያማ በሆነው መሬት ላይ በቀላሉ ሊሮጥ ይችል ነበር እግሮቹ ከተጎዱ ማንኛውም ወታደር ሊዋጋ አይችልም በመንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ ጫማችን የሚያመለክተው ወንጌል ወደ ሰዎች የምንወስድ መሆናችንን ነው የቤተሰባችን አባል ለሆነ ለጓደኞቻችን ለሌሎችም ሰዎች ስለ ኢየሱስ የምንነግራቸው ከሆነ ያኔ በቀላሉ አንሸነፍም ጳአንዴና ለመጨረሻ የሰይጣንን ግዛት የምንወርረውና ድል የምንመታውም ሰዎች በኢየሱስ አምነው የእግዚአብሔር መንግሥት ተካፋዮች እንዲሆኑ ስለ ኢየሱስ ስንመሰክርላቸው ነው መ በአጃችን ያኋምቷምፖ ጋጋጃሃ ጨብጠናል «ጋሻ» የሚለው ቃል የሚያመለክተው ርዝማኔውና ስፋቱ አንድን ወታደር ስለሚያህል በጣም ትልቅ ስለሆነ ጋሻ ነው የሮም ወታደሮች አንድን ከተማ ለማጥቃት ሲፈልጉ ከከተማው ቅጥር ግንብ የሚወረወርባቸውን ፍላጻዎች ለመከላከል እነዚህን መላ ሰውነታቸውን ሊሸፍኑላቸው የሚችሉ ጋሻዎችን ይጠቀሙ ነበር ልክ እንደዚሁ እምነት ከሰይጣን ፍላጻዎች ሊያድነን የሚችል ነው ይህ እምነት በተለይ መጀመሪያ ስንድን ያስፈለገን በኢየሱስ ሞት ያመንበትና የዳንበት እምነት ብቻ አይደለም ነገር ግን በየፅለቱ የሚያጋጥመንን ምንም ዓይነት ሁኔታ ለመቋቋም የሚያስችል በእግዚአብሔር ችሎታ ላይ የሚደገፍ እምነት ነው በምንታመምበት ጊዜ ወይም የምንወደው ሰው ሲሞትብን ወይም ደግሞ ስደት ሲነሣብን ሰይጣን ዓይኖቻችንን ከኢየሱስ ላይ ነቅለን ችግሮቻችን ብቻ እንድንመለከት ያደርገናል እንድንፈራ እንድንጠራጠር ወደ ዓለም እንድንመለስ ወይም እምነታችንን እንዳንጠብቅ ይፈልጋል ያለ እምነት አግዚአብሔርን ማስደሰት እንደማይቻል ያውቃል ዕብ እኛ ግን ኃያልና ልዑል ወደሆነው አምላካችን ማተኮር ይገባናል ሁኔታዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ናቸው በሚለው መተማመናችን ላይ መጽናት ይገባናል በመከራ ጊዜም ቢሆን አንድ ትንሽ ልጅ ስለ ልብሱና ስለ ምግቡ ሳይጨነቅ በወላጆቹ ላይ እንደሚተማመን ሁሉ እኛም እንዲሁ እግዚአብሔርን ልንተማመነው ይገባል የሰይጣን ጥቃት ምንም ይሁን ምን የምንተማመነው የምናሸንፍበትን ኃይል በሚሰጠን በአግዚአብሔር ላይ ነው ሠ የራስ ቁር የሮም ወታደርን ራስ አእምሮ ድርጊታችን ሁሉ ውስጥ ስለሆነ አስፈላጊ ነው አእምሮአችንን በደኅንነት መሸፈን አለብ ይህ ደኅንነት ደግሞ ሁለት ነገሮችን ሊያመለክት ይችላል አንደኛ ጳውሉስ እዚህ ላይ ሰይጣን የሚለውን የሚያደርገውንም ያድርግ እንጂ እኛ ማስታወስ ያለብን በኢየሱስ ስላመንን ድነናል ማለቱ ሊሆን ይችላል የእግዚአብሔር ልጆች ነን በእግዚአብሔር ተስፋዎች ላይ ተማመነ እን በችግሮቻችሁ ዙሪያ አትመልከቱ በኢየሱስ ባመናችሁ ጊዜ ለዘላለም ስለመዳናችሁ እግዚአብሔር የቃሉን ተስፋ ሰጥቶአችኋል ሁለተኛ ጳውሎስ የሚለው ሰይጣንን የምናሸንፍበት መንገድ እግዚአብሔር ስላዘጋጀልን እኛ አማኞች እርግጠኞች ሆነን መጽናት እንዳለብን ነውነ ድሉን ዛሬም በሰይጣን ላይ ተቀዳጅተናል ስለዚህ ሰይጣን ድል ይነሣናል ብለን ከመስጋት የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃሉች የእኛ አድርገን በሰይጣን ላይ ድል እንድንቀዳጅ እንዳደረጉን ማረጋገጥ ይኖርብናል በአእምሮአችን «ሰይጣን እያጠቃኝ ነው ባለፈው ጊዜ በወሲባዊ ኃጢአት ወድቄአለሁ ሰይጣንን የምቋቋምበት ኃይል የለኝም» ያልን እንደሆነ በሰይጣን እንደምንሸነፍ እርግጠኞች ሆንን ማለት ነው ዳሩ ግን «ሰይጣን እያጠቃኝ ነው በፊት በኃጢአት ብወድቅም ንስሐ ስለገባሁ እግዚአብሔር ይቅር ብሎኛል እግዚአብሔር ፍጹም እንደማይተወኝና እንደማይረሳኝ ቃል ገብቶልኛል ከሰይጣን ባርነት ነፃ እንደወጣሁ ነግሮኛ ል ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ ርዳታ ሰይጣንን ላሸንፈው እችላለ እግዚአብሔር ቅዱስ እንደሆነ እኔም እንደ እርሱ ቅዱስ እንድሆን ነግሮኛል በኛ ጴጥ ስለዚህ ሰይጣን ውሸቶችህን ላለመስማት አሻፈረኝ ብያለሁ ኢየሱስ ሆይ ንጽሕናዬን ጠብቅልኝ» ያልን እንደሆነ ያኔ የሰይጣንን ጥቃት እናሸንፈዋለን እንግዲህ የሰይጣንን ጥቃት ለማሸነፍ ዐቢይ መሣሪያችን የሚሆነው ኃይልን በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል ላይ መተማመናችን ነው ረ ሰይፍ ሰይጣንን በቀጥታ የምናጠቃበት መሣሪያችን ሰይፍ ነው ይኸውም የአግዚአብሔር ቃል ነው የእግዚአብሔር ቃል የተጻፈው በመንፈስ ቅዱስ ነው መጽሐፍ ቅዱስን እንድናስተውለው በሰይጣን ስንጠቃም ቃሉን እንድናስታውሰው የሚሜረዳንም አርሱ ነው እዚህ ላይ ጳውሎስ ሰይጣንን የምናጠቃው በጸሎት ነው አይለንም ይልቁንስ በሰይጣን ላይ ጥቃት የምንፈጽመው በእግዚአብሔር ቃል ነው ይለናል ለምሳሌ ሰይጣን ኢየሱስን ሲፈትነው የጠቀሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነበር ሉቃስ ስለዚህ ሰይጣን ለሚሰነዝረው ጥቃት ሁሉ የማሸነፊያው ምላሽ ደግሞ የሚገኘው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው ሰይጣንን «መቃወም» ማለት ይኸው ነው ሰይጣን እንዴት እንደሚያጠቃው እያንዳንዱ አማኝ ማወቁ በጣም አስፈላጊ ነው ከዚህ በኋላ ከመጽሐፍ ቅዱስ በቃላችን ያጠናነውን በመጥቀስ እግዚአብሔርን ለመተማመንና ለመታዘዝ መቁረጣችንን ለሰይጣን ውሸት የማንበገር መሆናችንን መንገር ለእያንዳንዱ አማኝ አጅግ አስፈላጊ ይሆናል ለሊ ጸሎት መንፈሳዊ ሕይወታችንን የሚያበረታ ኃይል የምናገኘው በጸሎት ነው በጦሩ ግንባር ማንኛውም ወታደር ከአለቆቹ መሪዎቹ መገናኘቱ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው ምንም እንኳ እንደዚህ ያለው ግንኙነት ጠላቱን ለመዋጋት ቀጥተኛ ድጋፍ ባይሰጠውም ጠላቱ በየትኛው በኩል በርትቶ እያጠቃ እንደሆነ አውቆ መቋቋም ይችል ዘንድ ቁልፍ የሆነ መሣሪያ ነው በዚህ ዓይነት ሕይወታችን በሞላ በአግዚአብሔር ላይ የጥገኝነት ባሕርይ ያለው ሊሆን ያስፈልጋል ይኸውም በጸሎት አማካኝነት መሆን አለበት ከዚህ የተነሣ ነው ጳውሎስ ስለ ሁሉም ነገር መጸለይ አለብን ያለው ጸሎት ለሰይጣን ጥቃት «ንቁዎች» እንድንሆን ይረዳናል እንዲሁም ደግሞ መሪያችን የሆነው ኢየሱስ ምን እያለን እንደሆነ ለማዳመጥ ያስችለናል እግዚአብሔር ራሱ በእኛ ሕይወት ውስጥ ሰይጣንን ለማሸነፍ የሚያስችለንን ሥራ እንዲሠራ ጸሎት ሕይወታችንን ትክክለኛ በአእግዚአብሔር ላይ መደገፍን ይሰጠናል ብዙ አማኞች ሰይጣንን የምንቋቋመው በጸሎት ነው ይላሉ ጳውሎስ ግን «ሰይጣንን በመቃወም ጸልዩ» አለማለቱ የሚገርም ነገር ነው የጸሎታችን ትኩረት ሰይጣንን በመቃወም ላይ ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር በምናቀርበው ልመና ላይ ነው መሆን ያለበት ለምሳሌ ጳውሎስ በተቻለው መጠን በነጻነት ወንጌልን ለማካፈል እንዳይችል ችሎታውን የገታበት ሰይጣን በጥረቱ ጳውሎስ እስር ቤት እንዲገባ በማድረጉ ሊሆን ይችላል ጳውሎስ ግን ከአስር ቤት በነፃ እንዲለቀቅ ሰይጣንን በመቃወም እንዲጸልዩለት አማኞችን አልጠየቀም ከዚሁ ይልቅ ጳውሎስ አማኞቹ እንዲጸልዩ የጠየቃቸው በእስር ላይ ቢሆንም በነጻነትና በግልጽነት ስለ ኢየሱስ እንዲናገር ድፍረት እንዲሰጠው ነው ሐዋርያት ስደት ባጋጠማቸው ጊዜ የጸለዩት የሰይጣንን ጥቃት በመቃወም ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል እንዲናገሩ እንዲያውጁ እግዚአብሔር ድፍረት እንዲሰጣቸው ነበር የሐዋ ስንጸልይ አብዛኛው ጸሎታችን አንዳችን ስለ ሌላችን የምንጸልየው ጸሎት መሆን ይኖርበታል እንዲሁም እንደ ጳውሎስ ትክክለኛ ስለሆነው ነገር ሁሉ እንዴት መጸለይ እንዳለብን ማጥናት ማወቅ ያስፈልገናል እርሱ የጸለየው የሰዎች መንፈሳዊ ሕይወት ብርታትን አንዲያገኝ እንጂ ጸሎቱ አምብዛም እግዚአብሔር በምድራዊ በረከት እንዲባርካቸው ወይም የተደላደለ ምቹ ኑሮን እንዲሰጣቸው ወይም ከገቡበት መከራ ውስጥ እንዲያወጣቸው አልነበረም ኤፌ ፊልጵ ጦር ፅቃችንን እንደለበስን በግልጽና በድፍረት ለኢየሱስ እንኖር ዘንድ ስለሌላው እንድንጸልይ ጳውሎስ ያበረታታናል አማኞች በሰይጣን ላይ ምን ሥልጣን አላቸው። ብለው በመጮኽና በመጥራት ከአደጋው የሚተርፉ ይመስላቸዋል ዳሩ ግን ሊያተርፈን የሚችለው የአርሱን ስም አጠራራችን ሳይሆን ከራሱ ከኢየሱስ ጋር ያለን የቅርብ ግንኙነት ነው ማሳሰቢያ በአንዳንድ አገሮች ኢየሱስ የሚለው ስም የሰዎች ተራ መጠሪያ ስም ሆኖአል ሆኖም ግን ሰይጣን አይፈራቸውም መጽሐፍ ቅዱስ «በኢየሱስ» ስም እንድንጸልይ ሲያዝዘን ሁለት ነገሮችን እየገለጥን ነው አንደኛ የጸሎታችን መሠረት ምክንያቱ የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በኢየሱስ ኃይል ላይ መሆኑን እያሳየን ነው ሰይጣንን « የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ በአንተ ላይ ሥልጣን ስላለው መታዘዝ ይገባፃል» አያልነው ነው ኢየሱስ በሁሉም ላይ ሥልጣን አለው ስለሆነም ሰይጣን የሚፈራው ያንን የቃላት ድምፅ አይደለም ይልቅስ ሰይጣን መፍራትና መታዘዝም ያለበት የኢየሱስን ትእዛዝ ነው ምክንያቱም ኢየሱስ በመስቀሉ ላይ በሞተ ጊዜ ሰይጣንን አሸንፎታልና ነው ሁለተኛ «በኢየሱስ ስም» ማለታችን ለመጸለይና ሰይጣንን ለማዘዝ ሥልጣን ያገኘነው ከኢየሱስ ጋር ካለን ግንኙነት የመነጨ መሆኑን ለመግለጽ ብለን ነው እርሱ ጌታችን ነው እኛ ደግሞ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ነን በእርሱ ፈንታ እንድንሠራ መብት ሰጥቶናል ሥልጣናችን አንደ አንድ አምባሳደር ነው አምባሳደር የገዛ ራሱ ሥልጣን የለውም ሥልጣኑ እርሱን ከወክለው አገር መሪ የመጣ ነው ቃሉ ንግግሩ ሥልጣን የሚኖረው መሪውን ወክሎ ሲናገር ብቻ እንጂ የራሱን አስተያየት በሚሰጥበት ጊዜ አይደለም እንደዚሁም ደግሞ በጸሎት ጊዜ የምንላቸው ቃላት ጠይም በሰይጣን ላይ የምንሰነዝራቸው ትእዛዛት ኃይል የሚኖራቸው ኢየሱስን ወክለን ስንናገራቸው ብቻ ነው ለኢየሱስ አየታዘዝን የማንኖር ከሆነ ወይም ቅዱስ ኑሮን የማንኖር ከሆነ ኢየሱስን ወክለን ወይም በእርሱ ሥልጣን አይደለም የምንጸልየው ማለት ነው ከኢየሱስ ጋር የቅርብ ግንኙነት ሳይኖራቸው ጳውሎስን በመኮረጅ ለመገሠጽ የሞከሩትን ሰዎች አጋንንት አላዳመጧቸውም ደበደቧቸው እንጂ የሐዋ ከኢየሱስ ጋር ትክክለኛ የሆነ ግንኙነት ከሌለን የእኛ ጸሎትም ሆኖ ትእዛዝ ተግሣጽ ምንም ኃይል አይኖረውም አማኞች ሰይጣንም ሆነ አጋንንትን ወደ ጥልቁ ጉድጓድ ለመጣል ምንም ሥልጣን የላቸውም የመጨረሻው ዘመን አስኪመጣ ድረስ ሰይጣን እንደማይታሰር መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስተምረናል እርሱን ለማሰር ኃይልና ሥልጣን ያለው ደግሞ ኢየሱስ ብቻ ነው በጸሎት ጊዜ ሰይጣን ሳይታሰር ታስሯል ብሎ ማለቱ የሐሰት ስሜትን በአማኞች ልብ ውስጥ ከማሳደሩም ሌላ መጽሐፍ ቅዱስን የተመረኮዘ ጸሎትም ስላልሆነ ዋጋ ቢስ ጸሎት ነው እየተቃወምን ልንጸልይበት የሚገባ የስካር መንፈስ ወይም የንዴት መንፈስ» ወይም «የመለያየት መንፈስ አንዳለ መጽሐፍ ቅዱስ በፍጹም አይነግረንም ሰይጣን ማንንም አንዲሰክር ወይም እንዲናደድ ወይም ከሌሎች ጋር ተጋጭቶ እንዲኖር ሊያስገድድ አይችልም ይልቅስ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያሳየው ስካር ወይም ንዴት ወይም ጠብ ለመሳሰሉ ኃጢአቶች አማኞች ራሳችን ተጠያቂዎች መሆናችንን ነው ሰይጣን እነዚህን ድርጊቶች ያበረታታል አጋንንትም አማኞች በእነዚህ ኃጢአቶች እየተሸነፉ እንዲፄዱ በርትተው ይጥሩ ይሆናል ነገር ግን መከራውን ያመጣብኝ እርሱ ነው ብለን በማመን አንድን ክፉ መንፈስ በመቃወም መጸለያችን ብቻ ነጻነት አያስገኝልንም ከዚህ ይልቅንስሐ ገብተን አኗኗራችንን መቀየር አለብን እንጂ በክርስቲያኖች ላይ የሚታየውን ኃጢአት በአንድ ርኩስ መንፈስ ላይ የማላከኩን አዝማሚያ ሰይጣን ስሰሚጠቀምበት ለኃጢአታችን ተጠያቂዎች መሆናችንን እንዳናስብና ተግባሮቻችንን እንዳንለውጥ ይከለክለናል አንድ ሰው በኃይል በሰይጣን መለከፉንና በቁጥጥር ሥር መዋሉን ካረጋገጥን ረጋ ባለ ሁኔታ ጉዳዩን ማጤን ይገባናል ለዚህም የሚከተሉትን ነገሮች ማስታወሱ ጠቃሚ ይሆናል ሀ ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት እስካለን ድረስ አጋንንቱን እንድንፈራ የሚያደርገን ምንም ምክንያት የለም ኢየሱስ ሰይጣንን አሸንፎታል ኢየሱስ ደግሞ በአርሱ ምትክ ሰዎችን ከሰይጣን ቁጥጥር ነፃ እንድናወጣቸው ሥልጣን ሰጥቶናል ማቴ የሐዋ ሰይጣንን እንድናሸንፈው ኢየሱስ ኃይሉን ሰጥቶናል ሉቃስ በዓለም ካለው ጋኔንም ይሁን ወይም ሰይጣን ይልቅ በእኛ ያለው ኢየሱስ ታላቅ ነው በኛ ። ብ ለሊ ከኢየሱስ ጋር ስላለን ግንኙነት ጤናማነት እርግጠኞች መሆን ይገባናል በሕይወታችን ውስጥ ያልተናዘዝነው ኃጢአት መኖር የለበትም ያልተናዘዝነው ኃጢአት ካለ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደ ሕይወታችን እንዳይጎርፍ ይገታዋል በኃጢአታችን አማካኝነት ሰይጣን በእኛ ላይ ኃይሉን ካጠናከረ ሌሎቹን ከእርሱ ተጽዕኖ ለማላቀቅ ኃይል አይኖረንም ሑሒ መንፈሳዊውን ውጊያ ብቻችንን መዋጋት የለብንም ሌሎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ አማኞችን ማሳተፍ ብልህነት ነው አንተ ጋኔን ያለበትን ሰው እያነጋገርከው ከሆነ ሌሎች ደግሞ እግዚአብሔር በኃይሉ እንዲሠራ ወደ እግዚአብሐር መጸለይ ይገባቸዋል መ ጋኔኑን እየተቃወምን በምንጸልይበት ጊዜ ሥልጣናችን ከኢየሱስ መሆኑን ለአጋንቱ ለመግለጽ መጽሐፍ ቅዱሳችንን በሚገባ መጠቀም አለብን ኢየሱስ በአጋንንት ላይ ያለውን ሥልጣኑን መሠረት በማድረግ ጋኔኑ ሰውዬውን እንዲለቅቀው እናዝዘዋለን መሥ ጋኔኑ ከለቀቀው በኋላ ሰውዬውን በሁለት መንገዶች ልናማክረው ይገባል አንደኛ ያላመነ ከሆነ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኙ እንዲያምን ልንመክረው ይገባናል መንፈስ ቅዱስ ወደ ልቡ ይመጣና ጋኔነ ድጋሚ እንዳይመለስበት መከላከያ ያበጅለታል መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ልቡን ካልሞላው ግን በፊት ከነበረበት በባሰ ሌላ ጋኔን ሊይዘው ይችላል ማቴ ሁለተኛ አማካሪው ከዚህ በፊት ሰይጣን ሰውዬውን ባሪያ አድርጎ ሲይዘው የተጠቀመባቸው ነገሮች ካሉ በአጠቃላይ ሁሉንም ማስወገዱን ማረጋገጥ አለበት እነዚህም የአስማተኝነት ክታብ ወይም ጨሌ ወይም ወላጆቹ ለሰይጣን አምልኮ ይገለገሉባቸው የነበሩት ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ ወይም ደግሞ የሚያዳምጠው ዘፈን ወይም ለሰይጣን ተጽዕኖ በርን የሚክፍቱ እርሱ የሚመለከታቸው ቪዲዮዎች ወይም መንፈሳዊ ለመምሰል በልሳን መናገር ወይም መንቀጥቀጥ የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላሉ ማንኛውም ሰው በሆነ መንገድ እግዚአብሔርን ካለመታዘዝ ድርጊት የተነሣ ሰይጣን እንዲቆጣጠረው በር ካልከፈተለት በስተቀር አብዛኛውን ጊዜ ሰይጣን በሰውዬው ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድርበት ሁኔታ ሊያገኝ አይችልም ብዙ ጊዜ ሰይጣን በር ሊያገኝ የሚችለው በሐሰት አምልኮ አማካኝነት ነው ጠላታችን ሰይጣንና በሚሊዮን የሚቆጠሩ አጋንንት እግዚአብሔርንና ልጆቹን እየተዋጉ ናቸው ኃይለኞችና ብልዛተኞችም ናቸው እግዚአብሔር በቃሉ እንደገለጸልን በጥንቃቄ ካልተዋጋናቸው እነዚህ መናፍስት ጠላቶቻችን ያሸንፉናል በዚሁ ታላቅ ጦርነት ድል ሊመጣ የሚችለው በእግዚአብሔር መንገድ መሠረት ስንዋጋ እንጂ በእኛ መንገድ ስንዋጋ አይደለም አንደኛ ከኢየሱስ ጋር ያለን ግንኙነት ከኃጢአት ነዓ መሆኑንና ከእርሱ ጋር ያለን ኅብረት ደግሞ በጸሎትና የእግዚአብሔርን ቃል በማጥናት እያደገ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባናል እርሱ ባዘጋጀልን ኃይል ብቻ ስንዋጋ ነው ልናሸንፍ የምንችለው ሁለተኛ ሰይጣንና አጋንንት አብዛኛ ውን ጊዜ እንዴት ሊያሸንፉን እንደሚችሉ ለይተን ለማወቅ ማጥናት ይገባናል መንፈሳዊ ሐቆች በሚመስሉ ግን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ በሆኑ ነገሮች ሰይጣን እያታለለን መሆኑን ለማወቅ ዘዴዎቹን ፈላልገን ማግኘት አለብን ሰይጣን ዓለምንና የኃጢአት ተፈጥሮአችንን ተጠቅሞ ስሕተት የሆኑ ነገሮችን እንድንፈጽም ለማድረግ ወይም መልካም የሆነውን ነገርም ቢሆን እግዚአብሔር በማይወደው መንገድ እንድናደርግ እንዴት እንደሚፈታተነን መገምገም ያስፈልገናል ሦስተኛ እግዚአብሔር ያዘጋጀልንን የጦር ፅታ በየቀኑ መልበሳችንን ማረጋገጥ ይገባናል እንግዲህ ወንድሜና እኅቴ ሆይ በዚሁ ማረጋገጫ መሠረት ወደ መንፈሳዊ ጦርነት ሂዱና ዝመቱ።