Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ስለ ደም የቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ ምንድን ነው። የደሙ ኃይል ሙሉ በረከት ከከበረው ፍሬ ጋር ያለው ከክርስቶስ ጋር በፍጹም አንድነት በመኖር ውስጥ ነው ሥራውን ከሠሪው እና ደሙን ከክርስቶስ የሚለየው የአኛ አለማመን ብቻ ነው። በደሙ ላይ አለመጠን ማክረር ተገቢ አይደለም አለበለዚያ ወደ ዘመናዊነት አመለካከት ተለውጦ ለሰዎች ትርጉም የማይሰጥ ይሆናል የሚል አስተሳሰብ አሰ እኔ ግን በዚህ ሐሳብ እንደማልስማማ መግለጽ እፈልጋለሁ እኔ ደም የሚለውን ቃል የተቀበልኩት ከሐዋርያው ዮሐንስ ሳይሆን ከክርስቶስ ከራሱ ነው።
መጥምቁ ዮሐንስ ስለክርስቶስ መምጣት ሲናገር ሁለት አገልግሎቶችን እንደሚፈጽም መግለጡን ማስታወስ ተገቢ ነው መጀመሪያ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ አለ ቀጥሎ በመንፈበ ቅዱስ የሚያጠምቅ ሲል ተናገረ መንፈስ ቅዱስ ከመውረዱ ወይም ከመፍስሱ በፊት የእግዚአብሔር በግ ደም በቅድሚያ መፍሰስ ነበረበት ብሉይ ኪዳን ስለ ደም ያስተማረው ይህ ነገር ፍፃሜ ካገኘ በቷላ እርሱን ተከትሎ የመንፈስ ቅዱስ መፍሰስ ፍፃሜ አግኝቷል ጌታ ኢየሱስ የመስቀል ላይ ሞቱ ወደዚህ ዓለም የመጣበት ዋናው ዓላማ መሆኑን በመግለጽ ተናግሯል ይኸውም ሕይወት የመዋጀት ጉዳይ ዋና ነገር እንደሆነ አመልክቷል ከመስቀል ሞቱ ጋር አያይዞ የእርሱ ደም መፍሰስ አስፈላጊነቱን በግልጽ ተናግሯል በቅፍርናሆም ምኩራብ ውስጥ ስለራሱ ሲናገር የሕይወት እንጀራ ብሎ ነበር ስለ ሥጋው ሲገልጽ ደግሞ ስለ ዓለም ሕይወት የሚሰጠው እንጀራ ሥጋው እንደሆነ ተናግሯል ከእራት ጊዜ በላይ በአጽንኦት ደሜን ካልጠጣችሁ በራሣችሁ ሕይወት የላችሁም ደሜን የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራስሁ በማሰት ገልጂዷል ዮሐ ጌታችን ኢየሱስ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነና የእኛን የጠፋ ሕይወት ወደ ስፍራው ስመመስስ የመምጣቱን መሠረታዊ ዓላማ ተናግሯል ይህም የሆነው ለእኛ በመሞት ደሙን በማፍሰስ እንዲሁም እኛን የደሙ ኃይል ተካፋዮች በማድረግ እንጂ በሌላ መንገድ አይደለም የብሉይ ኪዳን መስዋዕቶች ሰው በምትክ ሞት መኖር እንደሚችል በትንሣኤው ደግሞ የዘለዓለምን ሕይወት እንደሚያገኝ ያስተማሩትን ትምህርት ጌታችን ኢየሱስ አጽንቶልናል ጌታ ኢየሱስ በምድራዊ ሕይወቱ ማብቂያ ምሽት ላይ ታላቅ መስህብ ያለውን እውነት ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ በመስጠት የመጣበትን ትልቁን ሥራ ከመፈጸሙ በፊት ስለ ብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ በማለት የጌታን እራት ሥርዓት መሠረተ ማቴ ያሰ ደም መፍሰስ የኃጢአት ሥርየት ሊኖር አይችልም ዕብ ያለ ኃጢአት ሥርየት ደግሞ የዘለዓለም ሕይወት የስም ስለዚህ ደሙን በማፍሰስ ስእኛ አዲስ ሕይወትን አመጣልን በሚጠጣው ደሙ የራሱን ሕይወት ለእኛ አካፈለን ስሰ ኃጢአት ይቅርታ የፈስሰው ደሙ እኛን ከኃጢአት እዳ እና ከዘለዓለም ሞት ነፃ አደረገን ለበደላችን ሥርየት የፈሰሰውን ደሙን በእምነት ስንጠጣ የአርሱ ሕይወት በእኛ ላይ ይቆጠራል እርሱ ስለ እኛ ያፈስሰው ደሙ ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ የገባና የተሰጠ ነው በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት የሐዋርያት ትምህርት ጌታ ኢየሱስ ከትንሣኤውና ከእርገቱ በኋላ ለሐዋርያት በሥጋው ብዙም አልተገለጠም ቀደም ሲል በምሣሌነት ተገልጠው የነበሩት ሁሉ አለፉ ተሸፍነው በምሣሌነት ተጠቅሰው የነበሩት ጥልቅ መንፈሳዊ እውነቶች ደግሞ ተገሰጡ ደሙን የሜጋርደው ነገር አሁን ምንም አናይም። ምክንያቱም ከፍ ያለውን ስፍራ ይዞ የሚገኘው እርሱ ነውና ጌታ ኢየሱስ ሲመጣ የሚሻረውን የመቅደስ አገልግሎት የሚገልጸውን የዕብራዊያንን መልዕክት በቅድሚያ እንመልከት ይህ መልእክት በአጋጣሚ ሳይሆን ሆን ብሎ በዓላማ የተጻፈ ነው በየትኛውም ሁኔታ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን መንፈሳዊ ዓላማ በጥልቀት እንዲገለጥ ከተፈለገ የክርስቶስ ደም በቅድሚያ ስለዚህ እውነት አዲስ ነገር እንዲያስተምር መጠበቅ አለቦት የጌታችን የኢየሱስን ደም በሚመሰከት ከዕብራዊያን መልዕክት የሚከተሉትን እናነባለን ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ የክርስቶስ ደም ህሊናችሁን ያነፃል ዕብ ወንድሞች ሆይ በክርስቶስ ደም ወደ ቅድስት ለመግባት ዕብ ዐ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ሚሆን ወደ ኢየሱስ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል ዕብ ስለዚህ ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ ሕዝቡን እንዲቀድስ ከበር ውጪ መከራን ተቀበለ ዕብ በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነው ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው ዕብ ዐ በእነዚህ ጥቅሶች አማካይነት የክርስቶስ ደም የመዋጀት ማዕከላዊ ኃይል እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ ያስተምረናል ያለ ደም አልሆነም የሚሰው የዕብራዊያን መልዕክት አባባል በአዲስ ኪዳን የያዘውን ዋጋ ያህል በብሉይ ኪዳንም ይዚል። የክርስቶስ ደም የዘላለማዊነት ታላቅ ኃይና የመለኮት ጥበብ ጥልቅ ምስጢርም ነው ትርጉሙን በቀላሉ እንደምንረዳው አድርገን ማሰብ የለብንም እግዚአብሔር ራሉ የደሙን በረከትና ኃይል ለመግለጽ ለ ዐዐዐ ዓመታት ያህል ሰዎችን ሲያዘጋጅ ኖሯልፎ እኛም ጊዜ ወስደን በጥንቃቄ ልንመረምረው ይገባናል ትርጉም ያሰው እና ውጤታማ የሆነ ጊዜ ካልወሰድን እንዲሁ በእግዚአብሔር ፊት መቀመጥ ብቻውን ዋጋ የለውም የመስዋዕቱ ደም ማሰት መሠረታዊ ትርጉሙ ሕይወት ማቅረብ ማለት ነው እስራኤላዊ የሆነ ማንኛውም ሰው በምትኩ መስዋዕት የሚሆንሰትን ሕይወት እስካላቀረበ ድረስ ደም ከየትም ሊያመጣ አይችልም ጌታ ኢየሱስ እኛን ዋጋ ከመክፈል ነዛ አድርጎ ሕይወቱን ሰሞት አሳልፎ አልሰጠም ደሙንም አላፈሰሰልንም በፍፁም ይህን አላደረገም በአንጻሩ ግን የእኛን ሕይወት መስዋዕት መሆን የሚችልና ዋጋ ያለው አደረገው እንጂ በደሙ ውስጥ ያለው ስውር ዋጋ ግላዊ የመስዋእትነት መንፈስ ነው በተጨማሪም ያ ደም ሐሳብን ወይም አእምሮን በሚነካበት ጊዜ ግላዊ መስዋዕት የመሆንን መንፈስ ያመጣል ደሙ ባስገኘልን በአዲሱ ሕይወት ሙሉ ኃይል ውስጥ ማለፍ ከፈለግን ማንነታችንንና የገዛ ሕይወታችንን ሳይቀር መተውን መማር አለብን እነዚህን ነገሮች ከእግዚአብሔር ቃል በሚገባ ለመረዳት እንዲያስችለን ጊዜአችንን መስጠት ይኖርብናል። ደሙ ባለበት በዚያ የእግዚአብሔር የትንሣኤው ኃይል ወደ ዘለዓለም ሕይወት መግቢያ በሩን ይከፍታል ደሙ የሞትንና የሲኦልን ኃይል ወደ ፍጻሜ ማምጣት ችሏል የክርስቶስ ደም የፈጸመው ነገር ከለው መረዳት በላይ ነው የክርስቶስ ደም ሰማያትን ከፈተ በዕብራውያን ላይ ክርስቶስ የዘለዓለምን ቤባነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ የሚለውን ቃል እናነባለን በብሉይ ኪዳን የመገናኛ ድንኳን የተገለጠው የእግዚአብሔር መገኘት ከመጋረጃው በስተጀርባ እንደነበር እናውቃለን ያንን መጋረጃ አልፎ መፄድ የደፈረ ወይም መጋረጃውን ማስወገድ የቻለ የሰው ኃይል አልነበረም መጋረጃውን አልፎ ወደ ውስጠኛው ክፍል መግባት የሚችለው በዓመት አንድ ጊዜ ሏቀ ካህኑ ብቻ ነበር ይህም ሲሆን ደም ሳይዝ አይገባም አለበለዚያ የራሱን ሕይወት ያጣል መጋረጃው በሥጋ ላይ ተገልጦ ከእግዚአብሔር የለያየን የኃጢአት ምሣሌ ነበር የእግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ጽድቅ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንዳንገባ ስለ ከለከለን ማንም ሥጋ የለበሰ ወደ እርሱ መቅረብ አልተቻለውም አሁን ግን የእኛ ጌታ በቁሣዊ ነገር ሣይሆን በእውነተኛ መቅደስነት ተገለጠ እንደ ሊቀካህንና የራሱን ሕዝብ እንደሚወክል ሆኖ ስለ አዳም ኃጢአተኛ ልጆች በገዛ ደሙ ወደ ቅዱሱ እግዚአብሔር መገኛ መግቢያ ሲጠይቅ ይታያል እኔ ባለሁበት በዚያ እነርሱ ደግሞ ይሆናሉ የሚለው የአርሱ ጥያቄ ነው። ስለዚህ ነገር ሁላችን መልስ ልንሰጥ ያስፈልጋል የደሙ አስደናቂ ኃይል የተገለጠው በተለይ በምድር ላይ ለሚኖሩ ኃጢአተኞች ሲባል ነው ይህን በተመለከተ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተሰጡት ብዙ ምንባቦች ኛጴጥ ልዩ አጽንኦት ይሰጣል ቃሉም ከከንቱ ኑሮአችሁ በክቡር የክርስቶስ ደም እንደተዋጃችሁ ታውቃላችሁ ይላል መዋጀት የሚለው ቃል ጥልቅ ትርጉም ያለው ነው ይኸውም በመገዛት ወይም ነፃ በመውጣት ከባርነት መላተቅን የሚያመለክት ቃል ነው ምክንያቱም ኃጢአተኛው ጠላት በሆነው በሰይጣን ኃይል ሥርከሕግ እርግማን ሥር እና ከኃጢአት ኃይል በታች ባርያ ነው ስለዚህ በደም ተዋጅተዛሃል የሚለው አዋጅ ሊታወጀጅለት ያስፈልገዋል ይህም ደም ተራ ደም ሳይሆን የኃጢአትን ዕዳ መክፈል የቻለ የሰይጣንን ኃይል የደመሰስ እርግማንን እና ኃጢአትን ያወደመ ብርቱ ኃይል ነው ይህ አዋጅ በሚነገርበትና ተቀባይነት በሚያገኝበት ሥፍራ ሁሉ ከከንቱ ኑሮ እና ከኃጢአት ሕይወት መዋጀት እውነተኛ ሥራውን ይፈጽማል መዋጀት የሚለው ቃል እግዚአብሔር የኃጢአተኛውን ዕዳ ከመክፈል ጀምሮ እስከ ሙሉ ነፃ መውጣት ድረስ ያለውን የሥጋ ትንሣኤ የሚያጠቃልል ሰፊ ትርጉም አለው ኤፌዐ ሮሜ ጴጥሮስ ለመልእክቱ ተቀባዮች በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ይረጩ ዘንድ ለተመረጡት በማለት ጽፎላቸው እንመለከታለን ኛጴጥኹ ይህ ክፍል የክርስቶስ ኢየሱስ ክቡር ደም ልባቸውን በመንካት ወደ ንሥሐ እንዳመጣቸው እምነታቸውንም በውስጣቸው እንዳነሳሳ ነፍሳቸውን በሕይወትና በሐሴት እንደሞላ የሚያረጋግጥ ክፍል ነው። ራስህን ለእግዚአብሔር መንፈስ ምርኮኛ አድርግ የልብህን ዓይኖች በደሙ ላይ አድርግ ውስጣዊ ማንነትህን ለደሙ ኃይል ክፈት ራስህን በማያቋርጠው የመርጨት ደም ውስጥ አስጠልል በሰማይ በጸጋው ዙፋን ላይ ያለው ደሙ የአንተንም ልብ የአግዚአብሔር ዙፋንና መቅደስ አድርጐ ሊሰራው ይችላል ደሙ በአንተም ሕይወት ውስጥ ፍሬያማ እንዲሆን የእግዚአብሔርን በግ ጠይቀው ያን ግዜ ከክርስቶስ ደም ኃይል ጋር የሚወዳደር ምንም ነገር እንደሌለ አረጋግጠህ ያለ ጥርጥር አንተም መለማመድ ትጀምራለህ ምዕራፍ ሶስት በደም አማካይነት መታረቅ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተሥሪያ አድርጐ አቆመው ሮሜ በኢየሱስ ክርስቶስ የደም ኃይል ያገኘናቸውን የተለያዩ በረከቶች ስናስብ መዋጀት የሚለው ቃል ሁሉንም ያጠቃልላቸዋል ሆኖም ከነዚህ በረከቶች መካከል መታረቅ የመጀመሪያውን ስፍራ ይይዛል ስለዚህ እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው ይላል። ሚልኪ በውኃ በደም እና በእሳት መንጻት በአዲስ ኪዳን ሥር የሚከናወኑ የውስጣዊ ሕይወት መንጻት እና ከፃጢአት መውጊያ የመዳኛ ምሣሌዎች ናቸው በአዲስ ኪዳን መንጻት እንደ በረከት ነው የጠራ ወይም ንጹህ ልብ የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ ተጠቅሷል ጌታ ኢየሱስም ይህን አስመልክቶ ሲናገር ልበ ንፁሆች ብፁዓን ናቸው ብሏል ማቴ ሐዋርያው ጳውሎስ በኛ ጢሞቴዎስ ላይ ሲናገር ፍቅር ከንፁህ ልብ የሚወጣ መሆኑንና ስለ ንዑሕ ህሊናም ገልፆአል ጴጥሮስም የመልዕክቱን ተቀባዮች ብንዑሕ ልብ እርስ በእርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ ይላል አዚህ ላይ መንፃት የሚለው ቃል ሥራ ላይ ውሎ እአናያለን እግዚአብሔር በእምነት ልባቸውን ያነፃቸውና የእግዚአብሔር ሕዝብ ተብለው ስለተጠሩ ሰዎች ከቃሉ እናነባለን ሐዋ ጌታ ኢየሱስ የእርሉ ለሆኑት ያለውን ዓላማ ሲገለጽ መልካሙን ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነው ሕዝብ ለራሱ እንዲያነና ይላል ቆሮ እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሁሉ መንፃት በሰው ልብ ውስጥ የሚከናወን የኃጢአትን ይቅርታ የሚከተል ድርጌት መሆኑን ያስተምሩናል በኛ ዮሐንስ ላይ የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነፃናል የሚል ተጽፎልናል ያነዛል የሚለው ቃል በተለወጥንበት ግዜ የተቀበልነውን የኃጢአት ይቅርታ ፀጋ አያመለክትም ነገር ግን በብርፃን የሚሄዱ የእግዚአብሔር ልጆች የጸጋ ናሬ ነው እንዲሁም እርሱ በብርፃን እንዳለ በብርፃን ብንመላለስ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነፃል ይላል ከቁጥር በንላ ያለውን ፃሳብ ስንመለከት ከኃጢአት ይቅርታ በላይ እንደሆነ ያሳያል ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመዓም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው ይላል መንጻት የክርስቶስ ኢየሱስን የደም ኃይል በአማኝ ልብ ውስጥ በእምነት የሚቀበሉት ውስጣዊ ልምምድ እና ከኃጢአት ይቅርታ በኋላ የሚመጣ የኃጢአት ይቅርታ ፍሬ ነው በቃሉ መሠረት ይህ ድርጊት መጀመሪያ የሚከናወነው ሕሊናን በማንጻት ነው ነውር የሌለው ሆኖ በዘለዓለም መንፈስ ራሱን ለአግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነፃ ይሆን ይላል ዕብ የጊደር ሥጋ አመድ በረከሰው ላይ መረጨት የክርስቶስን ክቡር ደም በግል ለመለማመድ በምሣሌነት የቀረበ ነው ህሊና ለድርጊታችን ፍርድ የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን በተጨማሪም አግዚአብሔር ከእኛ ጋር ያለውን እኛም ከአግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ምስክርነት የሚሰጥ ውስጣዊ ድምጽ ነው ህሊና በደም በሚነፃበት ጊዜ እግዚአብሔርን ደስ እንደምናሰኝ ምስክር ይሆናል በዕብራውያን ዐ ላይ የሚያመልኩት አንድ ግዜ ነጽተው ከቪያ በኋላ በህሊናቸው ኃጢአትን ስላላወቁ ማቅረብን በተዉ አልነበረምን። ኃጢአት ከነመፈታተኛው አሁንም በሥጋችን ውስጥ ይኖራል ይሁን እንጂ እኛን የመግዛት ኃይል አይኖረውም ህሊና ሲነፃ በእኛና በእግዚአብሔር መካከል የሚጋርድ ትንሽ የኃጢአት ጥላ እንኳ ሥፍራ አይኖረውም በዚህ ጊዜ ጌታን በሙሉ የመዋጀት ኃይሉ መመልከት እንችላለን በደም የነፃ ህሊና ፍጹም መዋጀቱን እና የእግዚአብሔርን ፍጹም ደስታ ክመመስከር የሚበልጥበት ነገር የለም ህሊና ሲነፃ የህሊና ማፅከል የሆነው ልብም ይነፃል ልብ ከክፉ ህሊና መንጻት እንዳለበት ከዕብራውያን ዐ ተመልክተናል መንጻት ያለበት ህሲና ብቻ ሳይሆን ልብም ጭምር ነው ልብ ሲነፃ አአምሮአችንፈቃዳችንከፃሳባችንና ከምኞታችን ጋር አንድ ላይ ይነዛሉ ክርስቶስ ራሱን ለሞት አሳልፎ እስከ መስጠት ድረስ ባፈሰሰው ደሙ እንዲሁም ወደ ሰማይ በገባበት ኃይሉ የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤው በማያቋርጥ ሁኔታ ውጤታማ ሲሆኑ በሞትና በትንሣኤ ኃይሉ ክንውን ጠላትነትና የኃጢአት ምኞት ታረዱ የክርስቶስ ኢየሉስ ደም ከስውር እና ከልምምድ ኃጢአቶች ሁሉ ያነፃል ደሙ በነፍስ ውስጥ በሰማያዊ መንፈሳዊ ኃይል ሲሰራና በአንድ አማኝ ውስጥ የደሙ ሥራ በሙላት በሕይወቱ ሲገለጥ አዲሱ ልምምድ አሮጌው ተፈጥሮ ኃይሉን አንዳይገለጥ ይክከለክለዋል በደሙ ውስጥ ክፉ ምኞትና መሻት ይሸነፋሉ መንፈስ ቅዱስ የከበረውን የደሙን ፍሬ በሚገልጥበት ጊዜ ሁሰንተናን ያነፃል መሰናክል ቢከሰት እንኳ ነፍስ ቅጽበታዊ መንፃትና መታደስን ስታገኝ በንስሐ ያልተወገዱ ያልተነቃባቸው ኃጢአቶች በዚህ ሂደት ውስጥ ይከስማሉ በህሊና ክስ እና በኃጢአት ብክለት መካከል ልዩነት ያለ ቢመስልም ነገሩን የበለጠ በጠራ ሁኔታ ለመገንዘብ ያህል እንጂ በአውነተኛው ሕይወት ውስጥ ስንመጣ ግን እነዚህ ነገሮች በመካከላቸው የጐላ ልዩነት እንደሌለ እንረዳለን እግዚአብሔር በደም ውስጥ በኃጢአት ሁለንተና ላይ ይፈርዳል ሁሉም የደሙ እውነተኛ ሥራ ኃይሉን በሙላት በአንድ ጊዜ በህሊና ክስ እና በኃጢአት ብክለት ላይ ይገልጣል መታረቅና መንፃት ሁልግዜ ባለመነጣጠል አብረው ይሄዳሉ ደሙም ሳያቋርጥ ይሰራል ብዙ ሰዎች ደሙ ስለፈሰሰልን ደግመን ኃጢአት ብንሠራ እንኳ እንደገና ወደ ደሙ በመቅረብ መንጻት እንችላለን ብለው ያስባሉ ሀቁ ግን ከዚህ የተለየ ነው ደሙ እንደ ምንጭ ወይም እንደ ፏፏቴ የሚፈስሰው በውስጡ ወይም ከስሩ የሚሆኑትን ሰዎች ለማንፃት ነው ኃጤአትንና ርኩሰትን የሚያነፃ ምንጭ ተከፍቷል ዘካ የዘለዓለም መንፈስ ኃይል የሆነው የዘለዓለም ሕይወት በደሙ ውስጥ ይሠራል ስለዚህ ልብ ዘወትር በማያቋርጠውና በሚያነፃው የደም ፏፏቴ ስር ሊያድር ያስፈልገዋል በዘመነ ብሉይ ኪዳን መንፃት ለእያንዳንዱ ኃጢአት አስፈላጊ ነበር በአዲስ ኪዳን ግን መንፃት የተመሠረተው ዘለዓለም ህያው ሆኖ በሚኖረው በክርስቶስ ላይ ነው እምነት ይህንን እውነት ትኩር ብሎ በሚመሰከትበት በሚፈልግበት እና በሚያርፍበት ጊዜ ልብ በእያንዳንዱ ቅጽበት በደሙ ኃይል ጥበቃና ማንጻት ውስጥ ይኖራል የዚህን በረከት ሙሉ እርካታ መለማመድ በክርስቶስ ደም አማካይነት የተገኘውን የኃጢአት ሥርየት በእምነት ተካፋይ የሆነ ማንኛውም አማኝ ከመንጻቱም ውጤት ደግሞ ተካፋይ ይሆናል ነገር ግን የመንጻቱ ልምምድ በልዩ ልዩ ምክንያት የተሟላ ሆኖ አናይም። በተጓዳኝ ከደሙ ጋር ቅርብ ጥብቅ ግንኙነት አድርጐ የሚኖር ሰው የቅድስና ውጤቶች እንዴት እንደሚከሰቱ አናሳ መረዳት ቢኖረውም እንኳ በሚኖረው ቅርበትና ትስስር ምክንያት በደሙ የመቀደስ ልምምዱ ከዕለት ወደ እለት እየጨመረ ይሄዳል ነገር ግን ሁሉን ነገር አጠናቆ አውቆ መገኘት እንዳለበት ልንጠብቅበት አይገባም በእምነት ፀሎት ደሙ በውስጡ ታላቅ የመቀደስ ኃይሉን ሊገልጥ ይችላል በገዛ ደሙ ህዝቡን መቀደስ የሚችለው ጌታ ኢየሱስ ራሱ ነው በደሙ ወደ ራሉ ላቀረበው የእግዚአብሔር በግ በአምነት አምልኮ እና መቀራረብ ከልቡ ራሱን የጠሰ አማኝ ከመረዳቱ በላይ የሆነውን በደም መቀደስን ይለማመዳል ሰዚህ አማኝ ይህንን ነገር የሚያደርግለት ጌታ ኢየሱስ ራሱ ነው ነገር ግን አማኝ በእውቀትም ደግሞ ማደግ አለበት ወደ ተዘጋጀለት የበረከት ሙላት መግባት የሚችለው በዚህ መንገድ ነው ቅድስና የተፈቀደልን ነገር ብቻ አይደለም ነገር ግን በደሙ በረከትና በቅድስናችን መካከል ያለውን አስፈላጊ ትስስር ወይም ግንኙነት የማወቅም ኃላፊነት አለብን ጌታ ኢየሉስ ቅድስናውን በምን ዓይነት መንገድ በውስጣችን እንደሚሰራና በደሙ ቅድስና ያገኘንባቸውን ነገሮች ዓይነተኛ መለያ ማወቅ አለብን የቅድስና ሁሉ መጀመሪያ የእግዚአብሔር ለመሆን ለእግዚአብሔር መለየት እንደሆነ ተመልክተናል የኃጢአት ኃይል መሰበሩን ከኃጢአት እስራት መፈታታችንን ከእንግዲህ ወዲህ የኃጢአት ባሪያ አለመሆናችንን ነገር ግን በደሙ ነፃ ላወጣን ለአርሉ የተለየን መሆናችንን ደሙ አውጆልናል በዋጋ ተገዝታችኋል የራሳችሁ አይደላችሁም ይላል እኛ የእግዚአብሔር መሆናችንን የሚናገረው የደሙ ቋንቋ ይፄ ነው ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ የእርሱ እንድንሆን ይፈልጋል መርጦናል ገዝቶናልም በዙሪያቸው ካለው ነገር ተለይተው ለጌታ አገልግሎት አንደሚኖሩ ካህናት ደሙን በእኛ ላይ አይነተኛ መለያ አድርጎታል ይህ የመለየት ሃሳብ ብዙ ጊዜ ደጋግመን በጠቀስነው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ውስጥ በሚከተለው ሁኔታ በግልጽ ተቀምጧል ስለዚህ ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ ሕዝቡን እንዲቀድስ ከበር ውጭ መክራን ፕቀበለ እንግዲህ ነቀፌታውን እየተሸከምን ወደ እርሱ ወደ ሰፈሩ ውጭ እንውጣ በዚህ የምትኖር ክተማ የለችንምና ዕብ ከዚህ ዓለም ከሆነው ነገር ሁሉ መውጣት ቅዱስ የሆነ የነፃ ከኃጢአተኞች የተለየ የኢየሱስ ዓይነተኛ ዓላማ ነው የተከታዮቹም መለያ መሆን አለበት ውድ አማኝ ሆይ ጌታ ኢየሱስ በገዛ ደሙ ቀድሶፃል የቅድስናውን ሙሉ ኃይል እንድትለማመድ ይፈልጋል በደሙ በመረጨትህ ምክንያት በአንተ ውስጥ የሆነውን ነገር ለማወቅ ትጋ ቅዱሱ እግዚአብሔር ሙሉ በሙሱ የእርሱ እንድትሆን ይፈልጋል አንዳች ነገር ከእንግዲህ ወዲህ በአንተ ላይ አይሰለጥንም አንተም እንኳ በራስህ ላይ መብት የለህም እግዚአብሔር ለራሱ ለይቶሃል ምክንያቱም በአንተ ላይ ድንቅ ምልክት አድርጓል ያም ምልክት ከቡርና ድንቅ የሆነው በምድር እና በሰማይ የሚገኘው እርሱም የክርስቶስ ደም ነው የዘለዓለማዊው እግዚአብሔር ልጅ ሕይወት ያለበት በእግዚአብሔር የፀጋ ዙፋን ፊት የሚኖረው ነው ከኃጢአት ኃይል የመዋጀት ሙሉ ዋስትና የስጠህ የእግዚአብሔር ለመሆንህ ምልክት ይሆን ዘንድ በአንተ ላይ ተረጨ ውድ አማኝ ሆይ ስለ ደሙ የቀረበው ትምህርት ሁሉ ለከበረው ለዚህ ኑዛዜ እንዲያበቃህ ጸሎቴ ነው ጌታ ኢየሱስ በገዛ ደሙ ቀደሰኝ ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔር ነኝ ለማለት ያብቃህሽ ቅድስና ከመለየት በጣም የሚበልጥ እንደሆነ ተመልክተናል መለየት የቅድስና ጅማሬ ነው በተጨማሪም ደግሞ ግላዊ መሰጠት ከልብ እና በፍጽም ፈቃደኝነት ለጌታ ቅዱስ ፈቃዱ ለመኖር ምርኮኛ መሆን የቅድስና አንድ ክፍል መሆኑንም አይተናል የክርስቶስ ደም እኛን ምርኮኛ ለማድረግና ለመቀደስ በውስጣችን የሚሰራው በምን መንገድ ነው። መልሱ ከባድ አይደለም በሚቤዝንና ከኃጢአት ኃይል ነፃ በሚያወጣን በደሙ ኃይል መታመን ብቻ በቂ አይደለም ከሁሉም በላይ የዚህን ኃይል ምንጭ ማወቅና መጠቀም አለብን ደሙ ኃይል እንዳለው እናውቃለን ምክንያቱም ጌታ ኢየሱስ ራሱን በፈቃዱ ምርኮኛ አድርጎ በመስጠቱ ነው በፈሰሰው ደሙ ራሱን ቀደስ ለእግዚአብሔር እና ለቅድስናው ሙሉ በሙሉ ራሱን አሳልፎ ስጠ በዚህ ምክንያት ደሙ ቅዱስ ነው የመቀደስም ኃይል አለው በደሙ ውስጥ የክርስቶስን ሙሉ ምርኮኝነት እናይበታለን ደሙ ሁልግዜ ክርስቶስ መንገድ ከፋች ሆኖ ለከብ መሰጠቱን እና የኃይል ምንጭ እና በኃጢአት ላይ ድል አድራጊ ሆኖ መገለጡን ይናገራል ወደ ደሙ በቀረብን ቁጥር እና በመርጨት ደም ጥልቅ ዛሳብ ውስጥ ከኖርንና ከተመላለስን ለእግዚአብሔር ፍጹም ምርኮኛ በመሆን ከኃጢአት ሙሉ በሙሉ የመቤዝት መንገድ ነው የሚለውን የደሙን ድምጽ በጠራ ሁኔታ እንሰማዋለን የደሙ ድምጽ እኛን ለማንቃት ወይም ለማስተማር እንጂ በከንቱ አይናገርም ደሙ የሚናገረው በመለኮታዊና ሕይወት ሰጪ ኃይል ነው። ይኸውም በገዛ ደሙ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት ገባ ዕብ በዚህ መሠረት በእያንዳንዱ አማኝ ውስጥም ይህ እውነት ይሰራል ቃሉም እንዲህ ይሳል እንግዲህ ወንድሞች ሆይ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል አንድንገባ ድፍረት ስላለን ከክፉ ሕሊና ለመንፃት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን ዕብ ዐ በእነዚህ ሁለት ቁጥሮች ውስጥ የተጠቀሰው መግባት የሜለው ቃል ካህናት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡበት ዓምድ ሆኖ ያገለግላል በተመሣሣይ ሁኔታ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ በክህነት አገልግሎታችን ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ የታወጀልን በደሙ ኃይል ነው ስለዚህ ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን ይልና ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገን ይላል ራዕይ አለኝም እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አለ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል ራዕ በደሙ ኃይል ለእኛ ከተደረጉልን የከበሩ በረከቶች አንዱ ወደ እግዚአብሔር መገኛ ወደ ዙፋኑ መቅረባችን ነው ይህ የተባረከ በረከት ምን እንደሆነ መረዳት እንችል ዘንድ እስቲ ይህ የክቡር ደሙ ባርኮት በውስጡ የያዛቸውን ነገሮች በቅድሚያ እንገንዘብ ፀ መያመሬዖ ጳዳዘሴጨረ መሃ ዖመናዊ መሇሥ ጋ ፀ ሥሃያ መጋፈጎዎ መሰዎሪታ ጳሳድናፇረዝ ሕደረፇ ፀ ሪዕያ ደርሙ ኃይሳ ሐሴፊታም ሪፀረሶፉ ለመቭጣ በእግዚአብሔር መገኛ ውስጥ በትክክል መኖር ይህ አድል በተለይ በእስራኤል ለሚኖሩ ካህናት የተሰጠ ሆኖ በእግዚአብሔር መገኛ የመኖር ነፃ አድል እንደነበራቸው እናውቃለን። ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እናንተን ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ የደሙን ኃይል በውስጣችሁ እንደሚገልጠው ያለ ፍርሃት ተጠባበቁ ደሙ የፈሰሰው እኛን ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ለማድረግ ነው ደሙ በአንተ ውስጥ ሥራውን በመፈጸም ሙሉ ይሆናል ደሙ በእግዚአብሔር ዓይኖች ፊት በሰው ቋንቋ የማይነገር ብቃትና ክብር አለው በደም የሚረጨው የሥርየት መክደኛ የእግዚአብሔር የጸጋ ዙፋን መቀመጫ እና እግዚአብሔር ለመኖሪያነት የመረጠው ስፍራ ነው ለደሙ ሙሉ በሙሉ ምርኮኛ ወደ ሆነ ልብ በሙሉ ደስታና ሐሴት ይቀርባል ደሙ ማንም ሊቋቋመው የማይችለው ኃይል አለው። ከጌታ ከኢየሱስ ጋር ካለን ግንኙነት የተነሣ ለእኛም ወደ ቅድስት መግባት ተለጥቶናል ስለዚህ ኢየሱስ ወደ አብ እንዲህ በማለት ፀለየ እነሆኝ እኔም እግዚአብሔር የሰጠኝንም ልጆች ብ ኢየሱስ ታላቅ ካህን ነው የዕብራውያን መልእክት ኢየሱስ እውነተኛ መልከጸዴቅ እንደሆነ ያሳየናል ይህም ብቻ አይደለም ዘለዓለማዊ ልጅ ዘለዓለማዊና የማይለወጥ ክህነት ያለው ታላቅ ካህን ሆኖ በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጠ ይነግረናል በዚያ ለማማለድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል በተጨማሪም በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ሁሉ ሊያድናቸው ይችላል ኢየሱስ ታላቅና ኃያል ካህን ነው በእግዚአብሔር ቤት ላይ ታላቅ ካህን የሆነ ኢየሱስ በቅድስት አገልግሎት ሁሉ ላይ የተሾመ ነው የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ በእርሱ ጥበቃ ስር ይሆኑ ዘንድ ተሰጥተውታል ወደ ቅድስት ለመግባት የልብ መሻት ካለን እርሱ እኛን ለመቀበል በዚያ በሕይወት አለ በተጨማሪም ወደ አብ ያቀርበናል የመርጨትን ደም በእኛ ውስጥ የሚፈጽመው እርሱ ነው እርሉ በደሙ በኩል ገባ እኛንም በደሙ በኩል ወደ ቅድስት አስገባን በቅድስት ውስጥ ያለውን አገልግሎት እና እኛም ያለብንን ኃላፊነት ያስተምረናል ምንም እንኳ ደካሞች ቢሆኑ ጸሎቶቻችን መስዋዕቶቻችን እና አገልግሎቶቻችን ተቀባይነት እንዲኖራቸው የሚያደርገው እርሱ ነው ከዚህም በተጨማሪ በቅድስት ውስጥ ለሚኖረን አገልግሉትና ሕይወት ሰማያዊ ብርሃንና ኃይልን የሚሰጠን እርሱ ነው ሕይወትንና የቅድስናን መንፈስም የሚሰጠን እርሱ ነው ደሙ ወደ ቅድስት መግባትን እንደሰጠን ሁሉ መስዋዕትነቱ ይኸውም ሥጋው ደግሞ ሕያው መንገድን አስገኝቶልናል በቅድስት ውስጥ ከገባን በቷላ ጸንተን እንድንኖር ሁልግዜ እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን እንድንመላለስ ሊያደርገን የሚችለው እርሱ ነው ርህራፄን የተሞላ ታላቅ ሊቀካህን እንደመሆኑ እያንዳንዱን አማኝ እንዴት እንደሚያስተካክል ደካሞችንም እንዴት እንደሚረዳ ያውቃል በቅድስት ውስጥ ወደ እግዚአብሔር መቅረብን ውብ የሚያደርገው ይሄው ነው በዚያ ኢየሱስን በእግዚአብሔር ቤት ላይ ታላቅ ካህን ሆኖ እናየዋለን ቅድስት በጣም ከፍ ያለ እና ሊደረስበት የማይቻል መስሎ ሲሰማን የደሙ ኃይል ምን እንደሆነ መረዳት ያዳግተናል በተጨማሪም በአዲስና በሕያው መንገድ እንዴት እንደምንራመድ ማወቅ አንችልም በዚህን ጊዜ ወደ ቅድስት እንዲያመጣንና እንዲያስተምረን ወደ ሕያው አዳኝ እንመለከታለን እርሱ በእግዚአብሔር ቤት ላይ ታላቅ ካህን ነውና በእርሱ ከታመንክ ብቻ በቅድስት ውስጥ ትሆናለህ እንቅረብ እግዚአብሔር ለአኛ ያዘጋጀልንን ቅድስትን ነፃነትን የሰጠንን ደሙን ወደ ቅድስት የሚወስደውን ሕያው መንንድ እና እኛን የሚረዳንን ታላቁን ካህን ተመልክተን እንቅረብ አዎን እንቅረብ እግዚአብሔር ለእኛ ካዘጋጃቸው ከነዚህ አስደናቂ በረከቶች ምንም ነገር አይከልክለን ወደ ቅድስት መግባትን አግኝተናል። የልብ መንፃት የሚለው ቃል ከክፉ ሕሊና ለመንፃት ልባችንን ተረጭተን በማለት ተተርጉሟል በደም መረጨት አስፈላጊ ነው የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እንድታገለግል ሕሊናህን ከክፉ ሁሉ ያነፃዋል ኢየሱስ ወደ አብ በገባበት በደሙ ወደ ቅድስት እንደምንገባ ተመልክተናል ይሁን እንጂ ይህ በቂ አይደለም ሁለት ዓይነት መረጨቶች አሉ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ ካህናት በመሰዊያው ላይ በእግዚአብሔር ፊት በሚረጭ ደም ብቻ አይታረቁም ነገር ግን ስዎች ራሣቸው በደሙ መረጨት አለባቸው የክርስቶስ ደም በመንፈሰ ቅዱስ አማካይነት በቀጥታ ከልባችን ጋር መገናኘት አሰበት ከዚያ ልባችን ከክፉ ሕሊና ይነዛል ከዚያም በኋላ ሕሊና የኃጢአት ዕዳ ፈጽሞ እንደተከፈለ ምስክርነት ይሰጣል በእኛ እና በእግዚአብሔር መካከል የምትለያይ ትንሽ ነገር እንኳ መቅረት አትችልም የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ደስ እንደምናሰኝ ሕሊናችን ምስክር ይሆናል ምክንያቱም ልባችን ነጽቷል በመርጨት ደም በኩል ከእግዚአብሔር ጋር እውነተኛ ሕያው ሕብረት አድርገናል አዎን የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነፃል ከኃጢአት ዕዳ ብቻ ሳይሆን ከኃጢአትም ቆሻሻ ያነፃል በደሙ ኃይል ምክንያት የወደቀው አሮጌ ተፈጥሮአችን የራሱን ኃይል እንዳይገልጥ ይክለከላል ሣሩንና ልምላሜውን ሸፍናት የነበረው አቧራ በዝግታ የሚፈሰው ምንጭ አንጽቶ አዲስና መንፈስ ማራኪ እንደሚያደርገው ሁሉ ደሙም ያለ ማቋረጥ ልብን ለማንጻት ይሰራል ከደሙ ሙሉ ኃይል ሥር የሚናር ልብ ከክፉ ሕሊና የነፃ ወደ ፍጹም ነፃነት ለመቅረብ የተዘጋጀ ልብ ነው ሁለንተና ልብ ሁለንተና ውስጣዊ ተፈጥሮ በመለኮታዊ ሥራ ነጽቷል ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን የምንቀርበው በተረዳንበት እምነት ነው ልባችን እንደነፃ እንመን ደሙ እንደሚያነፃን በመታመን በእግዚአብሔር ፊት ክፍ ከፍ አድርገን እናክብረው ታላቁ ሊቀካህን በቅዱስ መንፈሱ አማካይነት በደሙ ነጽተን ወደ ቅድስት ለመግባት ሊያዘጋጀንና የቃሉን ትርጉምና ኃይል በመግለጥ ሊያስገነዝበን ይችላል ከዚህም በላይ ወደ ልባችን ለመግባት ያዘጋጃል ወደ ቅድስት ለመግባትና በዚያ ለመኖር የሚያስችል ልብ ማግኘት ምንኛ መታደል ነው ሰውነታችንንም ታጥበን ሰውነታችንን በጥሩ ውኃ ታጥበን እንቅረብ በሁለት ዓለሞች ውስጥ እንኖራለን እነርሱም የሚታየው እና የማይታየው ዓለም ናቸው ከሰው ጋር ግንኙነት የምናደርግበት ውጫዊ ወይም ቁሣዊ ሕይወት እንዳለን ሁሉ ከእግዚአብሔርም ጋር የሚያገናኝ ውስጣዊ ድብቅ ወይም ስውር መንፈሳዊ ሕይወት አለን። ቁሳዊው አካል ሰውነትን የሚወክል ከሆነ ሰውነት ውስጥ ያለውን ሙሉ ሕይወት ከተግባሮቹ ሁሉ ጋር ይወክላል ልብ በደም መረጨት አለበት ሰውነት ደግሞ በጥሩ ውዛ መታጠብ አለበት ካህናት ለእግዚአብሔር አገልግሎት ራሣቸውን ሲሰጡ ሰውነታቸውን በንጹህ ውሃ ይታጠባሉ በተጨማሪም በደም ይረጫሉ በጸ ዐ ወደ ቅድስት ውስጥ ሲገቡ በዚያ የሚያገኙት በመለዊያው ላይ ያለውን የሚረጭ ደም ብቻ ሳይሆን በገበታው ውስጥም ለመታጠቢያ የሚያገለግል ውዛ ተሞልቶ ያገኛሉ እንደዚሁም ደግሞ ክርስቶስ የመጣው በደምና በውነ ነው ዮሐ ስለዚህ በመደመሪያ በውሃ ተጠመቀ በኋላ በደሙ ተጠመቀ ሉቃ ዐ እኛ ደግሞ በውፃና በደም የምንነፃበት እጥፍ መንጻት አለን የውፃ ጥምቀት በንስሐ ከኃጢአት የመለየት ምሣሌ ነው ተጠመቁ እና ከኃጢአታችሁ ታጠቡ ደሙ ልብን ውስጣዊውን ሰው ሲያነፃ የውፃ ጥምቀት ግን ከኃጢአት መለየትን ለመመስክር ከሚታየው ሕይወቱ ጋር ሰውነትን መስጠት ነው ሰለዚህ ከክፉ ህሊና ለመንፃት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውፃ ታጥበን እንቅረብ ሥጋን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ካልነፃን የደሙን ውስጣዊ የማንፃት ኃይል መለማመድ አንችልም በመርጨት ደም የመንፃት መለኮታዊ ሥራ እና ከኃጢስት የመለየት ምሣሌ የሆነው የውዛ ጥምቀት የሚነጣጠሉ አይደሉም ወደ ቅድስት ለመግባት መንፃት አለብን ሳትታጠብ የንጉሱ መገኛ ወደሆነው ወደ ቅድስት መግባትን በፍጹም አታስብ ከኃጢአት ሁሉ ሳትነፃ ወደ እግዚአብሔር መኖሪያ ወደ ቅድስት መምጣት እንደምትችል ማሰብ ሞኝነት ነው የክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነፃል እግዚአብሔር የሜያነፃህን ኃይል ሰጥቶፃልና በቅድስት ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር የመኖር ፍላጎት ካለህ በእያንዳንዱ እርምጃህ ኃጢአትን የማስወገድ ጥንቃቄ ማድረግ አለብህ ያልተቀደሰ ሕይወት ወደ ቅድስት መግባት አይችልምና በቅድስት ውስጥ እንድንሆን የፈለገ እግዚአብሔር ይመስገን የእርሱ ካህናት እንደመሆናችን በቅድስት ውስጥ እርሱን ማገልገል አሰብን በቅድስት በረከት ይኸውም በቅዱሱ ሕብረት እንድንደሰት የልባችንን ንጽህና ይፈልገዋል በደሙና በመንፈሱ እንድንነፃ በተጠንቅቆልናል ስለዚህ ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንን በጥሩ ውፃ ታጥበን እንቅረብ እንቅረብ በጉባኤያችን ውስጥ ከልባቸው ወደ ጌታ ላልተመለሱት ሰዎች እንኳ የቅድስት ስፍራ ተዘጋጅቶላቸዋል መቅደሱም ደግሞ ተከፍቶላቸዋል ክቡር ደመ ሕያው መንገዱ እና ታላቁ ካህን የእነርሱ ናቸው በታላቅ ትምክህት እንቅረብ ብለን ልንጋብዛቸው ያስፈልጋል ከእግዚአብሔር የራቃችሁ ወዳጆቼ የእግዚአብሔርን አስደናቂ ፀጋ አታክፋፉ አስቸኳይ ጥሪውን ወደ እናንተ ወደ ላከው በልጁ ደም ዋጋ ወደ ቅድስት የሚወስደውን መንገድ መርቆ ወደ ከፈተው በቅዱስ መኖሪያው የእርሱ ልጆች አድርጎ በፍቅር እንደገና ለመቀበል ወደሚጠብቃችሁ ቅዱስ አባት ቅረቡ ወዳጆቼ እኔም ሁላችንም ወደ እርሱ እንቅረብ በማለት ልመናዬን አቀርባለሁ በእግዚአብሔር ቤት ላይ የሆነው ታላቁ ካህን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም የሆነ አዳኝ ነው እንቅረብ ጥሪው የቀረበው ለሁሉም አማኞች ነው በመቅደሱ ደጅ ላይ በመቆም አትርኩ የኃጢአትን ይቅርታ በልባችን ብቻ ተስፋ ማድረግ በቂ አይደለም ስለዚህ በመጋረሻው በኩል እንግባ ወደ አግዚአብሔር መንፈስ በእውነተኛ አቀራረብ እንቅረብ በእርሱ ቅዱስ መገኛ ውስጥ መኖሪያችንን እናድርግ ሰውነታችን የእግዚአብሔር ውስጣዊ መቅደስ ነውና በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ በአውነት ፈጽሞ ራሱን ለእግዚአብሔር የስጠ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ሙሉ የእምነት መረዳትን ይለማመዳል በቃሉም ውስጥ የተሰጡትን ተስፋዎች ሁሉ በደስታና በነፃ የራሱ አድርጎ ይወስዳቸዋል የእምነታችን ድካም መነሻው የራሳችን ልብ ጥመት ነው በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ አንቅረብ የዚያን ጊዜ በረከቱ የአኛ ይሆናል ደመ ፈጽሞ የኃጢአትን ይቅርታ ስላመጣና ኃጢአትን ስላሸነፈ አማኞች በነፃሣነት ወደ እግዚአብሔር እንዳይቀርቡ ወደ ኋላ ሊያደርጋቸው የሚችል ነገር የለም ከክፉ ህሊና ለመንፃት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንም በጥሩ ውፃ ታጥበን እንቅረብ ዘደሙ ፍጹም ኃይል እምነትን በልባችን እንቀበል ከቅዱስ ስናራ ጋር የማይስማማውን ማንኛውንም ነገር አውጥተን እንጣል ከዚያም በኋላ በየቀነ በቅድስት ውስጥ እንዳለን ይሰማናል ሕይወታችን በሆነው በክርስቶስ ውስጥ እኛም ደግሞ በዚያ ኑንሆናለን ከዚያን በኋላ ዘቅድስት ውስጥ ተግባራችንን ሁሉ ማከናወን እንጀምራለን የምናከናውናቸው እነዚህ ተግባራት ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ አግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙ መንፈሳዊ መስዋፅቶች ናቺው ወንድሞች ሁሆይ እግዚአብሔር በቅድስት ውስጥ እኛን እንደሚጠብቀን አውቀን ወደ እርሱ አንቅረብ እቅረብሇ የሚለው ቃል ከጸሉት ጋር የሚገናኝ ልዩ ጥሪም ነው እንደ ካህናት ዘመቅደሱ ውስጥ ሁልግዜ የማንኖርበት ጌዜ አለ ነገር ግን ነፍስ ፈጽሞ ወደ እግዚአብሔር ዘመመለስ ክእርሱ ጋር ብቻ በቃልኪዳን መተሳሰር ህብረት የምታደርግበት ገዜ አለ አብዛኛውን ጊዜ ጸሎታችን በደካማ ኃይል ከርቀት እግዚአብሔርን የሚጠራ መሆኑ የሜያሳዝን ነው እስቲ አያንዳንዱን ጸሎታችን እንመርምር በእውነት በቅድስት ውስጥ ሰለመሆናችን ይመሰክራል። ህብስቱን ስለመካፈል የተነገረው ሁሉ የክርስቶስን ደም በመጠጣት ሙሉ ገቢራዊነት ሊኖረው ይገባል ውጤቱ ከክርስቶስ ጋር ፍጹም የልብ ወዳጅነትና ፍጹም አንድነት የሚያመጣ ጥልቅ መንፈሳዊ ምስጢር ነው ነፍስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የክርስቶስን ደም ሙሉ ተካፋይ በምትሆንበት እና በፈሰሰው ደሙ የተገለጠውን ወዳጅነት በምትጋራበት ስፍራ ተግባራዊ ይሆናል ደም የሥጋ ሁሉ ሕይወት ነው ሕይወት ያለው በደም ውስጥ ስለሆነ ዘሌ አማኞች ከክርስቶስ ጋር አንድ አካል በሆኑበት ስፍራ ፍጹም በክርስቶስ ውስጥ የመኖር ከፍተኛ ፍላጐት አለ ደሙ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ለሰማያዊው ሕይወት ከሰው ችሉታ በላይ የሆነ ጎይልና ብርታትን ይሰጣል። በከፍተኛ ጉጉት የሚናፍቀው ሥጋና ደሙ ከሰማይ እንደሆነ ይገነዘባል መጠጣት ከሌሰ የሚጠጣ ነገር አስፈላጊ አይደለም ክርስቶስን እና ከእርሱ ጋር ያለውን ፍጹም ኀብረት በጉጉት መጠበቅ ደሙን ለመጠጣት የተሻለ ዝግጅት ማድረግ ወይም መጠማት ነው የተጠማች ነፍስ ከሰማያዊ ሕይወት ሰጪ ውኃ ጠጥታ እንድትረካ የምትደረገው በመንፈስ ቅዱስ ነው ቀደም በሰን እንደተመሰከትነው የክርስቶስን ደም መጠጣት ሰማያዊ ምስጢር ነው የሁሉም ዳኛ የሆነው እግዚአብሔር እና የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ክርስቶስ ባለበት የመርጨት ደም አሰ ዕብ ከእኛ መረዳት በሳይ የሆነው በእርሱ ዘንድ ያለውን እውነት መንፈስ ቅዱስ ወስዶ ያስተምረናል የአካሉ ክፍል አነደመሆናችን ደሙን እና ሕይወቱን መካፈላችንን እና የደሙ ሕያው ኃይል በእኛ ውስጥ እንደተላሰፈ ከክርስቶስ ጋር ባለን አንድነት በኩል መንፈስ ቅዱስ የሚገልጥልን የክብር መረዳት ነፀብራቅ ነው ከምንጸልይበት ጊዜ ደሙን በእምነት እንደተቀበልንና እንደጠጣነው በማሰብ ሊሆን ይገባል። ዮሐንስም መልሶ ጌታ ሆይ አንተ ታውቃለህ በማለት መልስ ሰጠ ሽማግሌውም መልሶ እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል አለው ይህ ገለጻ የተለጠው ኩፋኑን ከበው ከቆሙት ሽማግሌዎች ከአንዱ ነው በሰማያዊ ክብራቸው ውስጥ ያሉትን የተዋጁትን ሁኔታ የሚመለከተው ይህ ገለፃ ትልቅ ትርጉም አለው የክርስቶስ ኢየሱስ ደም የኃጢአተኞች ተስፋ የሆነው በዚህ ዓለም ኃጢአትና ጦርነት ላይ ብቻ ሳይሆን በሰማይም እንደሆነ ከላይ የተመለከትነው ምንባብ ያስረዳል ጠላት ሁሉ ተገገር ሲሆን ያ ክቡር ደም የድነታችን መሠረት እንደሆነ ሰዘለዓሰም ግንዛቤ ያስገኛል ደሙ በእግዚአብሔር ዘንድ በሰማይ ኃይሉን መግለጥ ያለበት በታች በምድር ያለውን ኃጢአት ለመክደን ብቻ እንዳልሆነ መገንዘብ አለብን በደሙ ተዋጀው ሁሉ ድነቱን ሙሉ በሙሉ በደሙ እንዳገኘ ለዘለዓለም ለዴሙ ምሥጋናና ክብር ምስክር ይሆናል ድነታችንን ሙሉ በሙሉ በደሙ እንዳገኘን ግልጽ መረዳት ካሰን በመርጨት ደም እና በለማያዊ ደስታ መካከል ያለውን እውነተኛ እና ተገቢ ግንኙነት በተሻለ ሁኔታ መረዳት እንችላለን። ነቢዩ ኢሣያስ ጽዮን በፍርድ ከእርስዋም የሚመሰሱ በጽድቅ ይድናሉ ብሏል ትኢሣ ሐዋርያው ጳውሉስም ፀጋ በጽድቅ ምክንያት ነገሠ ብሏል ሮሜ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም የላከበት ዋና ዓላማ ይህ ነው ፀጋን አሳንሶ መንግሥተ ሰማይ የመግባትን መብት ለመናገር ከመድፈር ይልቅ መግባት የሰጠንን ታላቁን የክብር ፀጋ መመልክት እና ማክበር መልካም ነው ወደ መንግሥቱ የገባንበት ታላቁ የክብር ፀጋ አንዳንድ ጊዜ በቤተክርስትያን ውስጥ ከሚጠበቀው በታች ወርዶ ይገኛል ከጥቂት ቀናት በፊት ከሞት በኋላ ወደ መንግሥተ ሰማይ የመሄድ ተስፋ እንዳለው ይናገር ከነበረው አንድ ሰው ጋር ስንነጋገር ተስፋውን በምን መሠረት ላይ እንዳደረገ ጠየቅሁት በምንም ዓይነት ሁኔታ ስለ ሕይወቱ ግድየለሽ እንደማይሆን በራሱም ጽድቅ ላይ ፈጽሞ እንደማይደገፍ እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ ጌታን ለመፈለግና ፈቃዱን ለማድረግ የተቻለኝን ያህል ጥረት አደርጋለሁ እኔም መልሼ በቅዱሱ እግዚአብሔር የፍርድ ዙፋን ፊት ለመቆም መሠረት ሊሆንህ አይችልም ብዬ ስነግረው ወዲያውኑ ስለ እግዚአብሔር ምህረት አነሣብኝ እኔም መልሼ ከምህረት በላይ የሚያስፈልገው ነገር እንዳለ ይኸውም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግቦት ብቸኛ ዋስትናው የእግዚአብሔር ጽድቅ እንደሆነ ሲለማ አዲስ ነገር መሰለው ብዙዎቹ በእምነት መጽደቅ የሚለውን ስብከት መስማት ይፈራሉ ነገር ግን በእምነት ካልጸደቁ የዘለዓለምን በረከት መካፈል እንደማይችሱ ግንዛቤ የላቸውም ሙሉ መረዳት ሳይኖረው ስለ ክርስቶስ ምስክርነት ከሚሰጥ ይልቅ ነገር ግን የክርስቶስን መከራ እንዲረዳ የእግዚአብሔር መንፈስ ያበራለት ልብ መካከል ሰፊ ልዩነት አለ አንድ ኃጢአተኛ ለሞት ቀርቦ በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ ብዙ ገፆች ያሉት አንድ ትልቅ መጽሐፍ በገፆቹ ውስጥ የእርሱ በጣም ብዙ ኃጢአቶች መፃፋቸውን ተጠቆመና እንግዲህ ያለው ተስፋ ምን እንደሆነ ተጠየቀ እርሱም በቀኝ እጁ ጣት ወደ ግራ እጁ መዳፍ እያመለክተ በምስማር የተወጋ እጅ እንዳለ አሣየ ከተወጋው እጅ ውስጥ ደም እንደፈሰሰ አስቦ በመጽሐፉ ገፆች ላይ የተፃፉት ብዙ ኃጢአቶች በዚያ ደም እንደተደመስሱ ገለጸ የበጉም ደም የተስፋው መሠረት እንደሆነ አስረግጦ ተናገረ አማኝ ኃጢአተኛን የበጉ ደም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባትን ለጥቶታል የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ደሙን በማፍሰስ የኃጢአትን ቅጣት ተሸከመ በእኛ ቦታ ራሱን ለሞት አሳልፎ በመስጠት ሕይወቱን ለብዙዎች ቤዛ አደረገ በቪህ ምክንያት የኃጢአት ቅጣት ተከፈለ የኢየሱስ ደም ቤዛ ሆኖ ሰለፈሰሰ በሰማይ በእግዚአብሔር ፊት ለኃጢአት ይቅርታ የፈሰሰ ደም ሆኖ ወደ ዙፋኑ ቀረበ። የኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወት ኃይል በደሙ ውስጥ ይሰራል ከአርሱ ጋር ለኃጢአት ሞተናል በደሙ በኩል ባለን የእምነት ግንኙነት የኢየሱስ የሕይወቱ ኃይል ወደ ውስጣዊ ተፈጥሮአችን በኃይል ዘልቆ ይገባል ደሙ የኃጢአትን ኃይል ይስብራል ከኃጢአትም ሁሉ ያነፃል ደሙ ማንጻት ብቻ ሣይሆን ይቀድሳልም መንጻት የድነት አንዱ ክፍል እንደሆነ ተመልክተናል ይህም የኃጢአት መወገድ ማሰት ነው ደሙ ከዚህም የበለጠ ነገር ያደርጋል የእግዚአብሔር ርስት እንድንሆን አደረገን ኢየሱስ ደሙን ሲያፈስስ በውስጣችንም ያደረገው ይህንነ ነው አኛ ደግሞ በአውነት የተቀደስን እንሆን ዘንድ ደሙን በማፍሰስ ራሱን ስለእኛ ቀደሰ በዚያ ቅዱስ ደም ስንደሰት አና ራሣችንን ስንሰጥ ለእግዚአብሔር ፈቃድና ክብር ሙሉ በሙሉ ስንማረክ በጌታ ኢየሱስ ውስጥ የተገለጠው የመስዋዕትነትና በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ የመኖር ኃይል በአኛም ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል ራሳችንን ባዶ እና ምርኮኛ አንድናደርግ ደሙ ቀደስን ስለዚህ እግዚአብሔር እኛን ርስቱ በማድረግ ውስጣችንን ይሞላል አውነተኛ ቅድስና በእግዚአብሔር መያዝና መሞላት ነው ይህ ተግባር የሚከናጦነው በበጉ ደም ነው እኛም በማይነገር ሐሴት እግዚአብሔርን በሰማይ ለመገናኘት በዚህ በምድር እንዘጋሻለን ወደ እግዚአብሔር በመቅረብና ከእርሱም ጋር ህብረት በማድረግ መደሰት ሰው ከአግቢአብኬር ጋር አንድ ዓይነት ፈቃድ የሚናረው ወይም ሰአግዚአብሔር መንግሥት ተስማሚ መሆን የሚመጣው ከእግዚአብሔር ጋር ኀብረት ከማድረግ ፍላጎትና ደስታ ነው በዚህ ውስጥ ደግሞ ጾሙጮ በምድር እያለን ለሰማይ አውነተኛ ዝግጅት አንድናዩርግ ኃይል ይሰጠጦናል ደሙ አንዴት ጠደ አግዚአብሔር አንዳቀረበን እና ወደ ክህነት አገልግሉት እንደሚመራን ተመልክተናል የእግዚአብሔር መገኛ ወደ ሆነው ወደ ቅድስት ለመግባት መኖሪያችንንም በዚያ ለማድረግ በደሙ ነፃነት አግኝተናል ደሙ በሚረጭበት ጊዜ የጸጋው ኩፋን በዚያ ይኖራል የሚለውን ታላቅ ሐሳብ ከደመ ጋር አያይዞታል ልባችን ከደሙ ሙሉ የሥራ ኃይል ሥር ሲቀመጥ የእግዚአብሔር መኖሪያ ይሆናል ያ ልብ ድነቱንም ይለማመዳል ደሙ ከእግዚአብሔር እና ከበጉ ከኢየሱስ ጋር የህብረት ልምምዱን እውን አደረገልን ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ ያለውን ቃል ረስተን ይሆን። ቃሉ በእግዚአብሔር መንፈስ የተመረጠ እንደሆነ ከልቤ አምናለሁ ደሙን ሕያው ያደረገውና የዘለዓለምን ሕይወት ኃይል ተሞልቶ የደሙ ዝማሬ ወደ እኛ እንዲመጣ ያደረገው መንፈስ ቅዱስ ነው ደሙ ከመረዳታችን በላይ የሆነ በረከትን ይዞ ወደ እኛ መጣ በአስተሳሰባችን ላይ የሚፈጠረር የተዛባ የደሙ አመለካከት ስንኩል የሆነ የሰው አተረጓጐም ውጤት ነው መንፈስ ሰአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ማወቅና መለማመድ የፈሰገ ማንም ቢኖር ቃሉ ከሰማይ እንደመጣ በእምነት ይቀበለዋል ሐሴትና የዘለዓለም ሕይወት ኃይል በውስጡ እንዳለበት ቃሉን በተለየ ሁኔታ ይረዳዋል ደሙ እና የበጉ ደም የሚሉት ቃሎች ቅድስትን የእግዚአብሔር የክብር ስፍራ እና አዲሱ ዝማሬ በታላቅ ሐሴት ለዘለዓለም የሚስተጋባበት አድርገውታል ለማያዊ ሐሴት በበጉ ደም በኩል በምድር ላሉት ባልተከፋፈለ ልብ ውስጥ ኃይሉን ይገልጣል በላይ በሰማይ ደግሞ በአአላፋት መካከል በዙፋኑ ዙሪያ የክብርን ሥፍራ ይሰጣቸዋል በመቤዝዢት ከእኔ ጋር ተካፋይ የሆናችሁ ወገኖቼ በሰማይ ያሉ በኩራት ስለ ደሙ ምን እና እንዴት እያሉ እንደሚዘምሩ የተረዳን ይመስለኛል ጌታ ኢየሱስ ያቀደልን እነዚህ መልካም ነገሮች በሕይወታችን ፍሬያማ እንዲሆኑ በታማኝነት አንጻልይ እውነተኛ ሰማያዊ ሕይወት ለመኖር በሙሉ የደሙ ኃይል ውስጥ መኖር አስፈላጊ ነው ደሙ ወደ ሰማይ መግባትን ሰጠን የማስታረቅ ደም በነፍስ ውስጥ በመሥራት በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ላሱት ሙሉ መረዳትን ይሰጣቸዋል ይህ ደም ወደ ቅድስት ውስጥ አመጣን ወደ እግዚአብሔርም አቀረበን ለመንግሥተ ሰማይም የምንበቃ አደረገን የሚቀድለው ደም ከክፉ ምኞትና ኃይል አዳነን በብርሃን ህብረት ለቅዱሱ የእግዚአብሔር ሕይወት ጠበቀን ደሙ ስማያዊ የምሥጋና ዝማሬን ሰጠን የወደደንና ራሱን ለእኛ የስጠን የበጉ ደም ለእኛ ብቻ ያደረገልንን ነገር አይናገርም በዋናነት ሁሉንም ነገር እንዳደረገ ይናገራል በከፍተኛ ደረጃ በደሙ ውስጥ የእርሱን ሕይወት ተካፋይነትን አገኘን በእምነትና ራሉን በመስጠት ደሙ ያደረገለት በሙላት መለማመድ የፈሰገ ብቻ በሰማይ ወዳለው የምሥጋና ዝማሬና ፍቅር የሚወስደውን መግቢያ ያገኛል በመቤዢዝት ከእኔ ጋር ተካፋይ የሆናችሁ የሰማይ አጋሮቼ ይህ ሕይወት ተረት አይደለም ለእናንተና ለእኔ የተዘጋጀ እውነት ነው ደሙ በመስቀሉ ላይ ብቻ ሳይሆን በዙፋኑም ላይ ታላቅ ክብራችን ነው ሕያው ወደ ሆነው ወደ በጉ ደም ምንጭ ውስጥ በጣም ጠልቀን እንግባ የበጉ ደም እንዲሰራ ልባችንን አስፍተን እንክፈትለት ታላቁ ዘለዓለማዊ ካህን ያለ ማቋረጥ በደሙ እንደሚያነፃን ከልባችን እንመን ከዚህ በፊት ያልተለማመድነውን የደሙን ኃይል እንድንለማመድ በሚቃጠል ፍላጎት እንጸልይ ለእግዚአብሔር ካህናት በመሆን በደምህ ዋጀኽን እያሉ ከሚዘምሩት ታላቅ ሠራዊት ጋር በሚበልጥ የሐሴት ዝማሬ እንቀላቀል በምድራዊ ሕይወታችን ይህንን ዝማሬ ያለማቋረጥ መዘመር አለበን እንዲህ እያልን ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገን ለእርሱ ከዘለዓለም እስክ ዘሰዓለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን አሜ።